የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ 1 ሺህ 400 የህግ ታራሚዎች በምህረት ተለቀቁ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/115178

ሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የነበሩ 1 ሺህ 400 ኢትዮጵያውያን የህግ ታራሚዎች በምህረት ለቀቀች።
Related image
በሳኡዲ ዓረቢያ መንግስት የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ከእስር የተለቀቁት ኢትዮጵያዊያኑ የረጅም ጊዜ ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩ ናቸው።

በተጨማሪም አሁን በእስር ላይ የሚገኙ ታራሚዎች የእስር ጊዜያቸው በ75 በመቶ እንደሚቀንስላቸው የሀገሪቱ ባለስልጣናት ማሳወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በምህረት ከተፈቱት መካከል 300 የሚሆኑት ዛሬ ሌሊት ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ መሆኑ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Related image
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.