የሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና ጽ/ቤት ተዘጋ!!!

Source: http://www.mereja.com/amharic/531500


የሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና ጽ/ቤት ተዘጋ!!!
(በሰማያዊ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)

ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ ሰማያዊን የማፍረሱን ተግባር አጠናቀው ለአምስት ዓመት ሲጠቀምበት የነበረውን አዲስ አበባ የሚገኘውን ዋና ጽ/ቤቱን አዘጉ፡፡
አህአዴግና ምርጫ ቦርድ በለየለት ሁኔታ ፓርቲውን ካፈረሱ በኋላ ህዝብን ለማጭበርበርና ለማደናገር ኢህአዴግ ጥቅሜን ያስከብሩልኛል ባለው ቅጥረኛ ቡድን በፓርቲው ውስጥ ምንም የተፈጠረ ነገር እንደሌለ ሁሉም የፓርቲው ተቋማት ስራቸውን አክብረው እየሰሩ እንደሆነና የ3.1 ሚሊዮን ብር የሩብ ዓመት በጀት እንዳፀደቀ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲያስነግር ከቆየ በኋላ ይህ ማጭበርበር እንዳላዋጣው ሲገነዘብ ሌላ ስልት በመቀየር ፓርቲው ለአምስት ዓመት ሲጠቀምበት የነበረውን ዋና ጽ/ቤቱን በመዝጋት ከመጋቢት 12 ቀን 2009 ዓ.ም ጅምሮ የስድስት ወር የቢሮ ኪራይ ሳይከፍሉ ፓርቲውን በዕዳ አስይዘው ዕቃውን ወደ አልታወቀ ቦታ እዲወሰድ ተደርጓል፡፡

ኢህአዴግ ሁለተኛውን አማራጭ ሊጠቀም የቻለው በተለመደው ፓርቲ የማፍረስ ስልት ሰማያዊን ለማፍረስ ያደረገው ደባ በሰማያዊ ቆራጥና እውነተኛ አባላት የተለያየ ኮሚቴዎችን በማቋቋምና እነዚህን ኮሚቴዎች የሚቆጣጠርና የሚከታተል ብሄራዊ ሸንጎ በማቋቋም ፓርቲያቸውን ወደ ቀድሞ ክብሩና ተቀባይነቱ ለመመለስ የሚያደርጉትን ጥረት በስጋት ስላየው መሆኑን ለማዎቅ ተችሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰማያዊ ቆራጥ አባላት የኢህአዴግ ሸፍጥ እና ሴራ ይህ ቡድን በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የሚቀጥልና የአገዛዙ የህልውና መሰረት መሆኑን በመገንዘብ የሰማያዊ ድርጅታዊ ነፃነትና ሙሉነት እስከሚከበር ድረስ ትግላቸውን በተጠና መልኩ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

Share this post

3 thoughts on “የሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና ጽ/ቤት ተዘጋ!!!

Post Comment