የሰኔ 15ቱ የግድያ ወንጀል ምርመራ መጠናቀቁ ተነገረ፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/168869

የሰኔ 15ቱ የግድያ ወንጀል ምርመራ መጠናቀቁ ተነገረ፡፡
የአማራ ክልል የሠላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር በፀጥታው ዘርፍ ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
(አብመድ) ሰኔ 15 2011ዓ.ም የተከሰተው የመሪዎች ግድያ ትልቅ ጠባሳ ጥሎ እንዳለፈ የገለጹት አቶ አገኘሁ በ2011ዓ.ም ዜጎች በሠላም የማይንቀሳቀሱበት ዓመት እንደነበርም ገልጸዋል፡፡ በወቅቱ የደረሰውን ችግር ለማለፍ ከክልሉ ሕዝብ ጋር በጋራ በመሆን የፀጥታ መዋቅሩን በማደረጃት ችግሩን ማለፍ እንደተቻለም አንስተዋል፡፡ ክልሉ በዚህ ወቅት ግን የተረጋጋ እንደሆነንና ከቁጥጥር ውጭ እንዳልሆነም አስታውቀዋል፡፡ አሁንም በክልሉ በግበዓት እና በሰው ኃይል አደረጃጀት በኩል ሥራዎች እንደሚያስፈልጉም ገልጸዋል፡፡

‹‹የክልሉ ችግር ውስጣዊና ውጫዊ ነው›› ያሉት አቶ አገኘሁ የውጩን ችግር ለመቋቋም የውስጥ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የክልሉን ሠላም ለማናጋት ‹ሌት ከቀን› የሚሠሩ አከላት እንዳሉ የገለጹት አቶ አገኘሁ በተለይም በለውጡ የተገፉ አካላት የሚፈጥሩትን ችግር ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመላተዋል፡፡
ከፌዴራል የፀጥታ ኃይሉ ጋርም በጋራ እየተሠራ እንደሆነና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙ እንሆነም አስታውቀዋል፡፡ ከሌሎች ክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተም በተለይም ከቤኔሻንጉል ጉሙዝ ጋር ያለው ቅንጅት መልካም እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ በቤኔሻንጉል ጉምዝ ክልል የጋራ ኮማንድ ፖስት በማቋቋም እየተሠራ እንደሆነ ገልጸው ከአፋር ክልል ጋርም ባጋራ እየተሠራ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ በቅርቡም ከአፋር ክልል መንግሥት ጋር የጋራ ምክክር እንደሚኖርም አስታውቀዋል፡፡
‹‹የቅማንት ብሔረሰብን የራስ አስተዳደር ጥያቄ አጀንዳ በሌሎች አካላት ተነጥቀን ለብዙ ችግር ተጋልጠናል›› ያሉት አቶ አገኘሁ ችግሩን ለመፍታት ሠላማዊ ውይይቶች እየተደረጉ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡ አብዛኛው የኮሚቴ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.