የሱዳን ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን አርባምንጭ ከተማ ገባ

የሱዳን ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን አርባምንጭ ከተማ ገባ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን ከገበታ ለሀገር ኢንቨስትመንት ጋር የሚተሳሰር ልማት ሥራ ላይ ለመሳተፍ አርባምንጭ ከተማ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አርባምንጭ ከተማ ሲገባ የጋሞ ዞን፣ የአርባምንጭ ከተማ እና የአርባምንጭ ዙሪያ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።
30 የሚሆኑ የሱዳን ባለሀብቶችን ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር በመተባበር ከገበታ ለሀገር ኢንቨስትመንት ጋር የሚተሳሰር ልማት ሥራ ላይ ለመሳተፍ ነው አርባምንጭ ከተማ የገቡት፡፡
ባለሀብቶቹ በዞኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ከጎበኙ በኋላ ለማልማት ፍለጎታቸውን ያሳያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጋሞ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

The post የሱዳን ባለሃብቶች የልዑካን ቡድን አርባምንጭ ከተማ ገባ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply