የሱዳን ጉዳይ እና የአገራችን ነገር ( መንግስቱ ዲ.አሰፋ)

Source: https://mereja.com/amharic/v2/108519

የሱዳን ጉዳይ እና የአገራችን ነገር ( መንግስቱ ዲ.አሰፋ)
Image result for sudan
የዛሬ 30 ዓመት በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጡት አዛውንቱ የሱዳን ርዕሰ ብሔር ዛሬ በሕዝብ ግፊት እና በመከላከያ ጣልቃ ገብነት ከሥልጣናቸው ወርደው የቤት ውስጥ እሥረኛ ሆነዋል።
አንዳንድ ጉዳዮች

የሱዳን ፖለቲካ መቀየር ወዴት እንደሚሄድ መገመት ይከብዳል። ለሁለት ዓመት የሚቆይ ወታደራዊ የሽግግር ሸንጎ በመቋቋሙ አገሪቷ ወደ ዴሞክራሲ የምታደርገው ጉዞ ለግምት አዳጋች ስለሚያደርገው። እስከዚያው ግን ለአገራችን ወሳኝ የሆኑ ገዳዮች ላይ ግንዛቤ እና ጥንቃቄ ያሻል።
1. ሊመጣ የሚችለውን ቀውስ ተከትሎ እና አገራችን በቅርቡ ባረቀቀችው የስደተኞች አዋጅ ተጠቅመው ብዙ የስደተኛ ጫና ሊደርስብን ይችላል። ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርም እንደዚያ።
2. የአልበሽር መንግሥት እጅግ ጠንካራ የሚባል ነበር። ያም ሆኖ ግን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር ወደ አገራችን ሲደረገ የነበረው በሱዳን በኩል ነበር። አሁን ደግሞ ያለውን አመቺ ሁኔታ በመጠቀም በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ይችላል። ጥንቃቄ ያሻል።
Image result for sudan
3. የሚመጣው መንግሥትም ሕዳሴ ግድባችንን በተመለከተ የሚይዘውን አቋም አናውቅም። ግድቡ ከሱዳን ድንበር 40 ኪሎሜትር ብቻ ነው የሚርቀው። መንግሥታቸው ወታደራዊ ነው።
ሌላው ቢቀር የችግሩ መንሥዔ ኢኮኖሚ መውደቅ በመሆኑ ሚመጣው መንግሥት ጠንካራ ናሽናሊስት የመሆኑ እድል ከፍተኛ ስለሆነ አዲስ የድርድር ቅድመሁኔታ ሊጠይቅ ይችላል። ከግብጽ ጋር የመወዳጀታቸው እድል ከፍተኛ ነው።
4. የዐረቡ ዓለም መንትያ ፖለቲካ (ሳዑዲ-ግብጽ-የዐረብ ኤሚሬቶች) እና (ኳታር-ኢራን-ቱርክ) ጎራ ጉዳይ። አልበሽር ለሁለተኛው ቡድን ያደላ ነበር። ይህ አሜሪካን አያስደስታትም። ኢሥራዔልንም አይመስጣትም። የኢሳይያስ አፈወርቂ የማይጨበጥ አቋም አለ። ሶማሊያን አለመዘንጋት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.