የሱዳን ፖለቲካዊ ቀዉስ በ አባይ ግድብ ላይ ተጽእኖ አያሳድርም ተባለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/111547
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/AA66C4AA_2_dwdownload.mp3

የሱዳን ፖለቲካዊ ቀዉስ ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ላይ በምታስገነባዉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ሥራ ላይ የሚያሳድረዉ ተፅዕኖ እንደሌለ የኢትዮጵያ የዉኃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚንስቴር አስታወቀ። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ሥለ ግድቡ ግንባታ በቅርቡ ሊያደርጉት የነበረዉ ዉይይት ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል። የሚንስቴሩ ባለሥልጣናት ዛሬ እንዳሉት ግን አዲሶቹ የሱዳን መሪዎች ሱዳን ሥለ ኢትዮጵያ የምታራምደዉ መርሕ እንደማይለወጥ ተናግረዋል። ባለስልጣናቱ አክለዉ እንዳሉት በግድቡ ሥራ ይሳተፍ የነበረዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ብረታብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ይዞት የነበረዉ ሥራ በሌሎች እስኪተካ ድረስ የግድቡ ግንባታ ተጓትቷል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.