የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለ2013 ዓ.ም 10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በጀት አፀደቀ

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለ2013 ዓ.ም 10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በጀት አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የ2013 ዓ.ም የክልሉ በጀት 10 ቢሊየን 725 ሚሊየን 142 ሺህ ብር እንዲሆን የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በጀቱ ከፌደራል እና ከውስጥ ገቢ የሚገኝ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል።

በቅርቡ በሀገሪቱ 10ኛ ክልል በመሆን የተዋቀረው የሲዳማ ክልል ምክር ቤት የመጀመሪያ ጉባኤውን ነው እያካሄደ የሚገኘው።

ምክር ቤቱ ዛሬ በሚጠናቀቀው ጉባኤው ከሰዓት በኋላም የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2013 ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር ሲሆን በተለያዩ አዋጆች እና ሹመቶች ላይም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

The post የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ለ2013 ዓ.ም 10 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በጀት አፀደቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply