የሳዑዲ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ከአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ

Source: https://fanabc.com/2019/10/%E1%8B%A8%E1%88%B3%E1%8B%91%E1%8B%B2-%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%89%B5%E1%88%8D-%E1%88%98%E1%8A%A8%E1%88%8B%E1%8A%A8%E1%8B%AB-%E1%88%9A%E1%8A%92%E1%88%B5%E1%89%B5%E1%88%AD-%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%88%9C/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ካሊድ ቢን ሳልማን ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ እና መከላከያ ሚኒስትር ማርክ እስፔር ጋር  ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም  በሀገራቱ መካከል ስለሚኖረው ወታደራዊ ትብብር ዙሪያ እና በመካከለኛው ምስራቅ በሚስተዋለው የሰላምና ደህንነት ችግር ዙሪያ መምከራቸው ነው የተገለጸው።

በቅርቡ በሳዑዲ ዓረቢያ የነዳጅ ማጣሪያ ተቋማት ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ  ውጥረት መንገሱ ይታወቃል።

ሳዑዲ ዓረቢያ፣ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራትም ጥቃቱ በኢራን የተፈጸመ ስለ መሆኑ በቂ ማስረጃ እንዳላቸው ማስታወቃቸው ይታወሳል።

የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት ውይይትም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ይበልጥ ያተኮረ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።

በዚህ መሰረትም  በቀጠናው የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ሪያድና ዩናይትድ ስቴትስ በቅንጅት ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም በባህረ ሰላጤው የሚስተዋለውን የሽብር እንቅስቃሴ በጋራ ለመከላከልና የቀጠናውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተነግሯል።

ንጭ፦አልጀዚራ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.