የስራ ቋንቋ በጥናት ይመረጥ – ክፍል 1 የደቡብ አፍሪካ ተመክሮ #ግርማካሳ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/180518


በቅርቡ ይፋ የሆነው የብልጽግና ፓርቲ፣ ለጊዜው አምስት የአገራችን ቋንቋዎች፣ አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ሶማሌኛ፣ አፋርኛና ኦሮምኛ፣ የድርጅቱ የስራ ቋንቋ እንደሚሆን ገልጿል፡፡ የድርጅቱ መሪ ጠ/ሚ አብይ አህመድም ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎችም የፌዴራል መንግስት የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ድርጅታቸው እንደሚሰራ ማሳወቃቸው ይታወቃል፡፡
ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎችን የስራ ቋንቋ ይሁኑ ሲባል የሚነሱ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች አሉ፡፡ አንደኛው የፌዴራል የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ቋንቋዎች ሲመረጡ መመዘኛው ምንድን ነው የሚለው ነው ? ኢትዮጵያ ወስጥ ከሰማኒያ በላይ ቋንቋዎች አሉ፡፡ ሁሉም የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ካልተደረገ፣ የተወሰኑት ተመርጠው የተወሰኑት የሚቀሩ ከሆነ፣ በግልጽ ምክንያቶቹና መመዘኛዎቹ መቀመጥ አለባቸው፡፡
ያ ብቻ አይደለም መመዘኛው ፍትሃዊ ስለመሆኑ መረጋገጥ አለበት፡፡የተወሰኑ ቡድኖች፣ አመጽ ስለቀሰቀሱ፣ ወይንም ስላስፈራሩ፣ እነርሱ የሚናገሩት ቋንቋ ቅድሚያ የሚሰጠው ከሆነ፣ መስፈርቱ አመጽና ኃይል ነው ማለት ይሆናል። ያ ደግሞ ለዘለቄታው ችግር የሚፈጥር ነው። ምን ጊዜም በኃይልና በጉልበት በማስፈራራት የሚሆን ነገር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያይል ስለሚሆን። ቋንቋውን መጠቀም ከመግባቢያነቱ አልፎ ሌላ ትርጓሜ እንዲሰጠውም ስለሚያደርግ።
ሁለተኛው ጥያቄ የአፈጻጸም ጥያቄ ነው፡፡ አንድ ቋንቋ የፌዴራል የስራ ቋንቋ ሆነ ሲባል ምን ማለት ነው ? የቋንቋው ተናጋሪዎች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢዎች በቋንቋ የፌዴራል መንግስት አገልግሎት ያገኛሉ ማለት ነው ? ያ ካልሆነ ደግሞ “ የፌዴራል ሰራተኞች የፌዴራል ቋንቋዎችን ማወቅ ፣ ወይም በያንዳንዱ የፌዴራል መስሪያ ቤት ፣ በሁሉም የፌዴራል ቋንቋዎች ፣ ተገልጋይ ባይኖርም፣ ቋንቁዎቹን የሚናገሩ በእኩልነት መቀጠር አለባቸው” ማለት ነው ? እነዚህም ጥያቄዎች ግልጽ ምላሽና ጥናት የሚጠይቁ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.