የስብሃት ማፊያ ቡድን – “EFFORT” የማፊያ ቡድን ንብረት ስለሆነ መወረስ አለበት!

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75412

Seyoum Teshome

ክፍል 5፡ መቀሌ ላይ የመሸገው ህወሓት በሀገሪቱ የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ በማስቀጠል እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ዋና እንቅፋት ሆኖ ይቀጥላል። በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የብሔር ግጭትና ብጥብጥ በማስነሳት በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ያደርጋል። በተለይ በትግራይ ክልል ደግሞ ምንም ዓይነት የለውጥ እንቅስቃሴ እንዳይጀመር እንቅፋት ይሆናል። ከዚህ በተጨማሪ የስብሃት ማፊያ ቡድን ለኢኮኖሚ እድገት እና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዳይኖር ዋና ማነቆ ነው።
በመሰረቱ በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለውጥ ዘላቂነት የሚኖረው በኢኮኖሚው ዘርፍ ስር-ነቀል ለውጥና ማሻሻያ ሲደረግ ነው። ምክንያቱም በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የሚስተዋለውን ህገወጥ አሰራርና የጥቅም ትስስር ማስወገድ እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ የግድ አስፈላጊ ነው። ለዚህ ደግሞ የውጪ ሀገርና የሀገር ውስጥ ድርጅቶችና ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ለማድረግ የጉምሩክና ታክስ አስተዳደር፣ የመሬት፥ ብድርና የውጪ-ምንዛሬ አቅርቦት፣ የቢዝነስ ማበረታቻና ድጋፍ አሰጣጥ ረገድ የሚስተዋለውን አድሏዊ አሰራር መቀየር ይኖርበታል።
“የስብሃት ማፊያ ቡድን” ተከታታይ ፅሁፍ፦

ክፍል 1፡ ህወሓት – ጨቋኝ ቡድን ወይስ ወራሪ ጠላት?
ክፍል 2፡ ከህወሓት ወደ ትማሌሊ – ከታጋይነት ወደ ማፊያነት!
ክፍል 3፡ “የEFFORT” ትክክለኛ ባለቤት እና የህወሓት ዋና አለቃ ማን ነው ?
ከፍል 4: የማፊያዎች ስልት ወንጀል መስራት እና ወንጀለኞችን ማበረታታት ነው!

በተለይ ደግሞ ለአዳዲስ ኢንቨስተሮች እና ሥራ ፈጣሪዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠር፣ ድጋፍና ማበረታቻ ሊደረግላቸው ይገባል። አሁን ባለው ሁኔታ ግን ምቹ ሁኔታ የተፈጠረላቸውና ድጋፍና ማበረታቻ እየተደረገላቸው ያሉት የመንግስት የልማት ድርጅቶች እና ኢንዶውመንት ድርጅቶች

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.