የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በቁጥጥር ሥር ዋለ

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%8B%A8%E1%89%80%E1%8B%B5%E1%88%9E-%E1%8B%A8%E1%88%80%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%8A%A8%E1%8A%95%E1%89%B2%E1%89%A3-%E1%89%A0%E1%89%81%E1%8C%A5%E1%8C%A5%E1%88%AD-%E1%88%A5/
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 33 ሰዎች በተከሰሱበት የክስ መዝገብ ለአንድ ዓመት በፖሊስ ሲፈለግ የነበረው የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ቴድሮስ ገቢባ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
 
ተከሳሹ ከሰኔ 05 እስከ 12 2010 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የወላይታና ሲዳማ ብሔሮችን በማጋጨት ለሰው ሕይወት መጠፋት እና ንብረት መውደም እንዲከሰት የዕርስ በርስ ግጭት በማነሳሳትና በመጠንሰስ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተከሶ ሲፈለግ የቆየ መሆኑ ይታወሳል፡፡
 
ከአንድ ዓመት በኃላ የፌዴራል ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነሃሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ተከሳሹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 13ኛ የወንጀል ችሎት ሆሳዕና ተዘዋዋሪ ችሎት መቅረቡን ከፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.