የቀድሞ ደህንነት መስሪያ ቤት ይጠቀምባቸው የነበሩ ንብረቶች የደረሱበት አይታወቅም

Source: https://mereja.com/amharic/v2/190493

የቀድሞ ደህንነት መስሪያ ቤት ይጠቀምባቸው የነበሩ ንብረቶች የደረሱበት አይታወቅም
“የቀድሞ ደህንነት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስልጣን ይጋፉ ነበር”
“የፀጥታ ተቋማት በፖለቲካ ሽግግር ውስጥ” በሚል ርዕስ፤ በስትራቴጂያዊ ጥናት ተቋም አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በተካሄደው ሴሚናር ላይ ከለውጡ በኋላ ሁሉም የፀጥታ ተቋማት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆነው እንዲሠሩ የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እየሆነ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን፤ ብሔራዊ ደህንነትም የራሱን የደህንነት ማሠልጠኛ ኮሌጅ መክፈቱ ተነግሯል፡፡
የሀገሪቱ የፀጥታ ተቋማት ከሪፎርሙ በፊትና በኋላ ያላቸውን ጥንካሬና አሠራር በገመገመው በዚህ ሴሚናር ላይ፤ ምሁራን፣ የመንግስት አማካሪዎችና ወታደራዊ አመራሮች ምልከታቸውን አጋርተዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጐበዛይ፤ ከሪፎርሙ በኋላ በፀጥታ ተቋማት ላይ የተደረጉ ለውጦችን በዝርዝር ያስረዱ ሲሆን፤ ስለ ብሔራዊ ደህንነት ያለንን የአመለካከትና የአስተሳሰብ መዛባት በማረቅ ላይ ያተኮረ ለውጥ እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቀድሞ የደህንነትና ፀጥታ ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይፈፀሙ እንደነበር፣ ከህግና መመሪያ ውጪ በርካታ ተግባራት ይከናወኑ እንደነበር እንዲሁም ዝቅተኛ ሙያዊ ብቃት እንደነበርና በዋናነትም መንግስትን ከህዝብ የመጠበቅ ተልዕኮን አንግበው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አስረድተዋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ግንባታ ሠነዶችም ሠራዊቱን የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ጠባቂ አድርጐ የሚያስቀምጡ ነበሩ ብለዋል – ሚኒስትር ዴኤታው፡፡
እነዚህን ግምገማዎች መነሻ ባደረገው የሪፎርም ሂደትም፤ የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ መሠራቱን በዚህም መንግስት ዜጐችን ሊያጠቃ ይችላል ከሚል መነሻ ዜጐችን ከመንግስት ጭቆና ማዳንን የአስተሳሰቡ ማዕከል ያደረገ የደህንነት ተቋም ለመገንባት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
መከላከያ ሠራዊቱም ሀገርን ከውጭ ጠላት መከላከል ብቻ ሳይሆን ዜጐችን ከመንግስት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.