የቅማንት ጉዳይ! – (ሙሉቀን ተስፋው )

Source: https://mereja.com/amharic/v2/73401

የቅማንት ጉዳይ! (ሙሉቀን ተስፋው )

የትሕነግ ቅጥረኞች በአካባቢው ሕዝብ ላይ ያደረሱት ጥፋት ቀላል እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ከዚህ በኋላ ግን ይህ ጥፋት አይቀጥልም፤ በፍጹም አይቀጥልም። ለጠፋው ንብረት፣ ያለአግባብ ለተሰዉ ወገኖቻችን እናዝናለን)) ከባለፈው ጥፋት መማር ግድ ይለናል።
የቅማንት ጥያቄ የሕዝቡ አይደለም። በ69ኙም ቀበሌዎች ሪፈረንደም ቢደረግ በእርግጠኛነት 10 ፐርሰንቱም ይህን ጉዳይ አደግፈውም። ይህን የምለው ዝም ብዬ አይደለም። የቅማንትን ጉዳይ ከ2002 ዓም ጀምሮ ስከታተለው የቆየሁት ከሕዝቡም ጋር የጠበቀ ግንኙነት ስላለኝ ነው።
በአማራ ተጋድሎ ወቅት ቀኝ እጄ ሆኖ በእጅጉ ከፍተኛ የማስተባበር ሥራዎችን ሲሰራ የነበረው ከጅማ ጀምሮ የማውቀው ዘመን የማይለውጠው ጓደኛዬ ቅማንት አማራ ነው። ይህ ልጅ በአማራ ተጋድሎ ምክንያት ታስሯል፤ ፓስፖርቱን ተቀምቶ የውጭ ጉዞው ታግዷል፣ የሙሉቀንን መረጃ ሽጥልን ተብሎ በትሕነግ ደኅንነቶችም ብዙ ብዙ ስቃይ ደርሶበታል፣ ሕይወቱም ተመሰቃቅሏል፣ ከዚህ ወንድሜ የበለጠ የአማራ ታጋይ አላውቅም። ይህ ወንድሜ የቅማንት ኮሚቴ ነን በሚሉ በትሕነግ ቅጥረኞች ብዙ ማስፈራራት ደርሶበታል። ወንድሙ ተገድሎበታል። ብዙ ብዙ።
ወደጎንደር ብቅ ባልኩ ቁጥር ሁሌም የግድ የምጠይቃቸው ቅማንት ቤተሰቦች አሉኝ። እሱ ቅማንት አማራ ነው። ባለቤቱ ፋርጤ ነች። ልጆች ወልደዋል። በፍቅር አብረው ይኖራሉ። የእኔም ቤተሰብ ማለት ናቸው።
ከቅማንት ማኅበረሰብ መሪ አባ ወንበሩ መርሻ ጋር ብዙ ትውውቅና ውይይትም አድርጌ አውቃለሁ። የአባ ወንበሩ ቤተዘመዶች ጭልጋ ስሔድ በገጠሩም በከተማው ከቤታቸው እንደቤቴ ነው የምቆጥረው። ከቅማንት አማሮች ጋር በአጪሩ ያለኝ ግንኙነት የጠነከረ ነው። ይህን ተጠቅሜ ያለውን ቂምና በቀል ለመጨረሻ ጊዜ እንዲደርቅ የበኩሌን አስተዋጽኦ አደርጋለሁ።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.