የቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያን ቤተ ጊዮርጊስን በአረንጓዴ ብርሃን የማስዋብ መርሃ ግብር ተካሄደ

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%8B%A8%E1%89%85%E1%8B%B1%E1%88%B5-%E1%88%8B%E1%88%8D%E1%8B%AD%E1%89%A0%E1%88%8B-%E1%8A%A0%E1%89%A5%E1%8B%AB%E1%89%B0-%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%88%B5%E1%89%B2%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%89%A4%E1%89%B0/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቅርሶችን በአረንጓዴ ብርሃን የማስዋብ መርሃ ግብር በቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያን አንዱ በሆነው ቤተ ጊዮርጊስ ተጀምሯል።

የቤተ ጊዮርጊስን በአረንጓዴ ብርሃን የማድመቅ ስነ ስርዓቱ ከአየርላንድ መንግስት ጋር በተገባው ስምምነት መሰረት የተከናወነ መሆኑም ተነግሯል።

የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊዮ ቫራድካር ባሳለፍነው ጥር ወር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡ ቅርሶችን በአረንጓዴ ብርሃን ለማስዋብ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

በትላንትናው እለት ምሽት የዚሁ አካል የሆነው ቅርሶችን በአረብጓዴ ብርሃን የማስዋብ ስራ በቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያን አንዱ በሆነው ቤተ ጊዮርጊስ በአረንጓዴ መብራት የማድመቅ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።

በስነ ስርዓቱ ላይም በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የባህል ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ገብርኤል አስፋው፣ የቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያናት ዋና አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ፅጌ ስላሴ መዝገቡ፣ የላልይበላ ከተማ ከንቲባ እና በኢትዮጵያ የአየርላንድ አምባሳር ተገኝተዋል።

በአክሱማዊት ገብረህይወት

Share this post

One thought on “የቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያን ቤተ ጊዮርጊስን በአረንጓዴ ብርሃን የማስዋብ መርሃ ግብር ተካሄደ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.