የበላይ ዘለቀ ሽልማት ዕውቅናና ምሥጋና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 07/2013 ዓ.ም ባህር ዳር /// “አንድነት ለከተማችን ደብረማርቆስ እድገት” በሚል መሪ ሐ…

የበላይ ዘለቀ ሽልማት ዕውቅናና ምሥጋና መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 07/2013 ዓ.ም ባህር ዳር /// “አንድነት ለከተማችን ደብረማርቆስ እድገት” በሚል መሪ ሐሳብ 2ኛው ዙር የበላይ ዘለቀ ሽልማት የዕውቅናና የምሥጋና መርሐ ግብር በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ነው። ይህ መርሐ ግብር ለደብረ ማርቆስ ከተማ የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የላቀ አስተዋጾ ላበረከቱ የንግዱ ማኅበረሰብና ባለሀብቶች ዕውቅና የሚሰጥበት ነው። ለከተማዋ ገጽታ ግንባታም የላቀ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦችም ይመሠገኑበታል። በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ተመሥገን ጥሩነህና የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወርቀሰሙ ማሞን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፤ የደብረ ማርቆስ ከተማ የሕዝብ ተወካዮችና ባለሀብቶችም ተገኝተዋል። በላይ ዘለቀ የተሰኘው የዕውቅናና ምሥጋና መርሐ ግብር በ2012 ዓ.ም ነበር የተጀመረው። ምንጭ:- አብመድ

Source: Link to the Post

Leave a Reply