የቡርቃ ዝምታ፡ የአቶ አዲሱ አረጋ ትችት እና የተስፋዬ ገብረዓብ ምላሽ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/111554

BBC Amharic ከቀናት በፊት የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝቦች የትስስር መድረክ ተብሎ በተዘጋጀው መድረክ ላይ የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ የሰጡት አስተያየት በማኀበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።
አቶ አዲሱ እና ተስፋዬ
በመድረኩ ላይ አቶ አዲሱ፤ የልሂቃን እና የፖለቲከኞች የሃሰት ትርክት የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብን ለመከፋፈል ጥረት አድርጓል ብለዋል።
አቶ አዲሱ ”በልሂቃን እና በፖለቲከኞች የሃሰት ትርክት አማራ እና ኦሮሞ እሳት እና ጭድ ናቸው የተባለው የተዛባ አስተሳሰብ ነው። . . . እሳት እና ጭድ አይደለንም። አንዱን በዳይ ሌላውን ተበዳይ አድርጎ ለማቅረብ ከፍተኛ ገንዘብ ወጥቶ፤ በጀት ተመድቦ፤ ሆነ ተብሎ ሁለቱን ሕዝብ ከፋፍሎ በጽናት እንዳይቆሙ ለማድረግም በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ ነበር። ለአብነትም ‘የቡርቃ ዝመታ’ የተሰኘውን የተስፋዬ ገብረዓብን መጽሐፍ መጥቀስ ይቻላል” ሲሉ ተደምጠዋል።
አቶ አዲሱ እሁድ ሚያዝያ 13፣ 2011 ዓ. ም. ይህን ማለታቸውን ተከትሎ በርካታ የወቀሳ እና የድጋፍ ሃሳቦችም ተሰንዝረዋል።
አቶ አዲሱ ንግግሩን ባደረጉበት ምሽት እንዲሁም ትላንትናም (ሚያዝያ 14፣ 2011ዓ. ም.) በፌስበክ ገጻቸው ላይ ” ‘የቡርቃ ዝምታ’ መጽሐፍን በተመለከተ የሰጠሁት አስተያየት ብዙዎችን እንዳላስደሰተ ተረድቻለሁ። እኔ ማንሳት የፈለኩት ሃሳብ ጽሑፎች የሚቀርቡበት እና የሚተረኩበት መንገድ፤ ሕዝብ ከጨቋኝ ስርዓት ስር ለመውጣት የታገለውን፤ በሕዝቦች መካከል የተከሰተ ግጭት አድርጎ ማቅረብ በሕዝቦች የወንድማማችነት ግንኙነት ላይ ተጽእኖ ያሳድራል ለማለት ፈልጌ ነው።” በማለት የይቅርታ አድርጉልኝ መልዕክት አስፍረዋል።
በጉዳዩ ላይ አቶ አዲሱ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ” ‘የቡርቃ ዝመታ’ የተሰኘው መጽሐፍ ሙሉ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.