የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቀጣይ አካሄድ ምን መምሰል እንደሚገባው አመላካች የንቅናቄ ፕሮጀክት በየካ ክፍለ ከተማ አደራጆች ቀርቦ ከባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች፣ከአባላትና ደጋፊዎች…

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቀጣይ አካሄድ ምን መምሰል እንደሚገባው አመላካች የንቅናቄ ፕሮጀክት በየካ ክፍለ ከተማ አደራጆች ቀርቦ ከባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች፣ከአባላትና ደጋፊዎች ጋር ውይይት ተደረገበት። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ቀጣይ አካሄድ ምን መምሰል እንደሚገባው አመላካች የንቅናቄ ፕሮጀክት በየካ ክፍለ ከተማ አደራጆች ቀርቦ ከባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች፣ከአባላትና ደጋፊዎች ጋር ውይይት የተደረገበት መሆኑን የፓርቲው ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ያደረሰን መረጃ አመልክቷል። በባልደራስ የየካ ክፍለ ከተማ አደራጆች የቀረበው የፓርቲው ቀጣይ የንቅናቄ ፕሮጀክት ከአባላትና ደጋፊዎች በተጨማሪ ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የፓርቲው ፖለቲካ ዘርፍ ተጠሪ ኢንጅነር ጌታነህ ባልቻ እንዲሁም የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ ተገኝተውበታል። የባልደራስ የካ ክፍለ ከተማ አደራጆች ዛሬ መስከረም 24 ቀን 2013 ዓ.ም በክ/ከተማው ባካሄዱት የውይይት መድረክ በቀጣይ ፓርቲው ለማካሄድ ያሰበውን አገራዊ ንቅናቄ በተመለከተ ሰፋ ያለ አወያይ ፕሮጀክት እንደቀረበበት ነው ወግደረስ ጤናው የገለፀው። በመድረኩ የተገኙ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አደራጆች፣አባላትና ደጋፊዎችም በቀረበው ፕሮጀክት ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አንስተው ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በፕሮጀክቱ ከተነሱ ነጥቦች መካከልም በእስር ላይ ያሉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች(የህሊና እስረኞች) እንዲፈቱ መጠየቅ እና በቀጣይ ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ጠንካራ አደረጃጀትና የምርጫ ሰራዊት በመፍጠር ምርጫውን ለማሸነፍ መስራት የሚሉት ይገኙበታል። ባልደራስ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት በየ15 ቀናት በተለያዩ ክ/ከተሞች በየተራ የሚደረግ የውይይት መድረክ መሆኑን የገለፀው ወግደረስ ከአሁን ቀደምም የተወሰኑ ክ/ከተሞች ምክክር ማካሄዳቸውን ጠቅሶ በቀጣይም ወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ አጀንዳ በመቅረፅ የሚደረገው ውይይት ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያለው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply