የቤተ-ክህነት ፈተና – ፍትሕ መጽሔት

Source: https://mereja.com/amharic/v2/147266

በፍትሕ መጽሔት ቁጥር 44 እትም ላይ የወጣ ጽሁፍ
የቤተ-ክህነት ፈተና
Image may contain: textየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሀገረ-መንግሥቱን በማበጀቱ ሂደት የነበራትን የበዛ አበርክቶ መካድ አይቻልም። ጥንት መንግሥታዊ ተቋማት ባልነበረበት ጨለማ ዘመን፣ በተለያየ እርከን የሚያገለግሉ አስተዳዳሪዎችን በዕውቀት ገርታ ለፍሬ አብቅታለች። የተፃፈ ሕግ ባልረቀቀበት ወቅትም፣ በዳኝነት ሥራ ሊያገለግሉ የሚችሉ አዋቂዎችን ቀርጻ፣ በሥነ-ምግባር አንፃ ከጊዜው አኳያ የተሻለ ሥርዓት ለማንበር ታትራለች። በቤተ-መንግሥቱ ላይ ተጽዕኖዋ በበዛበት ገናና ዘመኗ፣ ከአገራቸው በኃይል ተገፍተው የተሰደዱ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን፣ ከተወነጨፈ ፍላፃ ከለላ እንዲያገኙ ተጽእኖ አድርጋለች።
የዴሞክራሲ ሽታ በማይታወቅበት፣ ባህላዊ ሥልጣኔ በነገሠበት ጥንታዊ ዘመን፣ ባህር አቋርጠው፣ ድንበር ተሻግረው የመጡ እንግዶች፣ እምነታቸውን እንደያዙ በነፃነት ይኖሩ ዘንድ መፍቀዱ የማይታመን መምሰሉ አስገራሚ አይደለም። ትምህርት ሚኒስቴር በማይታወቅበት ሺ ዓመታት፣ ኃላፊነቱን ተሸክማ ግዴታዋን ተወጥታለች። (መስሪያ ቤቱ የተመሰረተው በ1935 ዓ.ም እንደሆነ ልብ ይሏል።) ቅርስን፣ ታሪክን እና ትምህርትን በማስፋፋቱ ረገድ ቀዳሚና ብሔራዊት ተቋም እንደነበረች የሰነድ ማስረጃም ሆነ ህያው ምስክሮች አሉ። እንደ አህጉርም ሆነ እንደ ሀገር በተንሰራፋው ኋላቀርነት ምክንያት፣ የግሪክ፣ የሮማና የአይሁድ ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎች ለምዕራቡ ዘመናዊ ትምህርትና ሥልጣኔ እርሾ ሲሆኑ፤ አቻ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ፍልስፍናዎችና እሳቤዎች በ‹ጋን መብራት›ነት ተገተዋል።
በየአካባቢው ከታነፁ ቤተ-ክርስቲያናት በተጨማሪ፣ በተነጠሉ ሰዋራ አካባቢዎች የተመሰረቱት ገዳማት የምስጢረ ዕውቀት ማከማቻ ሆነው ዛሬ ድረስ ዘልቀዋል። አገር የሚያዘምኑ፣ ትውልድ የሚቀይሩ የልህቀት- መንኮራኩሮች አንድም ተሸሽገው፣ ሁለትም በአልቦ- ፈላጊነት እንደዋዛ ተረስተው ተቀምጠውባቸዋል። ማተሚያ ቤቶች ባልተቋቋሙበት እልፍ ዐመታት፣ አያሌ መነኮሳት መጽሐፍትን በራሳቸው መንገድ በሚፈጥሩት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.