የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የፀጥታ ሁኔታ

https://gdb.voanews.com/0398C7EB-BC8F-4CA2-84DA-22CBD6319DA9_cx0_cy5_cw0_w800_h450.png

በቤንሻጉል ጉምዝ ክልል በወንበራ ወረዳ ሰሞኑን ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ የፀጥታ ኃይል ወደ አካባቢው በመግባቱ አሁን ሰላማዊ እንቅስቃሴው የተረጋጋ እንደሆነ የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ጥቃቱ በማንነት ላይ ያነጣጠረ እንደነበረ አድርግው አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች መዘገባቸው “ስህተት ነው” የሚሉት የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ አጥቂዎቹ “ለውጡን የማይደግፉና ፀረ-ሰላም” ያሏቸው ኃይሎችና ሽፍቶች ሽፍቶች እንደሆኑ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply