የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እያካሄደ ያለው ሪፎርም ያከናወናቸውን ተግባራት ይፋ አደረገ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/184092

ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት በሪፎርም ስራዎች ያከናወናቸውን ተግባራት ይፋ አደረገ
የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እያካሄደ ያለው ሪፎርም ተልዕኮውንና የስራ ባህሪውን ግምት ውስጥ በማስገባት ግልፅነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት ፕሮፌሽናል ተቋም መመስረት ላይ ነው፡፡

የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤል የተቋሙ የ100 ቀን እቅድ አፈጻጸም በተገመገመበት መድረክ እንዳብራሩት፤ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ባካሄደው የሪፎርም ስራ ተቋሙን እንደገና ለማቋቋም የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ አጠናቋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፀደቀ በኋላ አሁን ያለው የተቋሙ ስያሜ በአዲስ የሚቀየር ይሆናል፡፡ አዋጁን መነሻ በማድረግም ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች እንደ አዲስ ተቀርጿል።
በተጨማሪም አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት የሚመራበት ስትራቴጂክ ዕቅድ የተጠናቀቀ መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነር ደመላሽ፤ ስትራቲጂክ ዕቅዱ ተቋሙ ከፖለቲካ ገለልተኛ፣ ብሄራዊ ጥቅምን እንዲሁም የህዝብን ሰላምና ደህንነት የሚያስከብር ትውልድ ተሻጋሪ ፕሮፌሽናል የመረጃ ተቋም እንዲሆን አቅጣጫ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
የብሄራዊ የደህንነት ስጋቶችን በተደራጀና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ለመከላከል የሚያስችል የብሄራዊ ደህንነት ስጋቶች ምላሽ አሰጣጥ ስርዓትን ጨምሮ ሌሎች ሰነዶችም ጭምር በሪፎርም ሂደቱ ተዘጋጅተው በተለያየ ደረጃ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
ባለፉት ወራት ተልዕኮውን የሚመጥንና ከታወቁ ዓለም አቀፍ አቻ የመረጃ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ የሚያደርገው አሰራርና አደረጃጀት ከመፍጠር አንፃርም በርካታ ስራዎች በሪፎርም ማዕቀፍ ስራ ተከናውነዋል፡፡ ለአብነትም በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ስጋቶችንና ሊፈጸሙ የሚችሉ አሻጥሮችን እንዲሁም ከባድ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈለጊ መረጃዎችን ለሚመለከተው አካል የሚያቀርብ የኢኮኖሚ ደህንነት ዋና

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.