የብሪታንያ ምክር ቤት እገዳን ተከትሎ በርካቶች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%8B%A8%E1%89%A5%E1%88%AA%E1%89%B3%E1%8A%95%E1%8B%AB-%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%88%AD-%E1%89%A4%E1%89%B5-%E1%8A%A5%E1%8C%88%E1%8B%B3%E1%8A%95-%E1%89%B0%E1%8A%A8%E1%89%B5%E1%88%8E-%E1%89%A0%E1%88%AD/

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 25 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን የብሪታንያ ምክር ቤትን ማገዳቸውን ተከትሎ በሺህዎች የሚቆጠሩ ብሪታኒያውያን ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ ወጥተዋል።

አዲሱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ምክር ቤቱን በመስከረም ወር እንዲተታገድ ማድረጋቸውን ተከትሎ የጀመሩትን ተቃውም በማጠከር ዛሬ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ያካሄዱት።

ሰልፈኞቹ የጠቅላይ ሚንስትሩ አካሄድ ዴሞክራሲን የሚገድል ነው የሚል መፈክር በመያዝ ጠቅላይ ሚንስትሩን ተቃውመዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን ውሳኔን በመቃወም እየተካሄደ ያለው የተቃውሞ ሰልፉ፤ በለንደን በስኮትላንድ፣ ዌልስ እና በሰሜን አየርላንደም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ውሳኔው ዴሞክራሲያዊ ሂደትን እና በህዝብ የተመረጡ የፓርላማ አባላትን መብት የሚጥስ እንደሆነ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።

ከቀናት በፊትም በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ብሪታኒያዊያን በተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመራቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.