የብአዴን እግድ መሠረተቢስ እርምጃ ነው ሲሉ አቶ በረከት ስምኦን አማረሩ!

Source: https://welkait.com/?p=16538

አቶ በረከት ስሞኦን ከብአዴን ከተባረ በኋላ በኢትዮጵያ የAP ጋዜጠኛ ከሆነው ከኤልያስ መሰረት ጋር የሚከተውን ቃለ ምልልስ አድርጓል!! ********** (Elias Meseret Taye for AP) ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር ያደረግኩት ቃለ መጠይቅ (ከእንግሊዘኛ የተተረጎመ): ጥያቄ:- በመጀመርያ ብአዴን ሰሞኑን እርስዎ ላይ ስለወሰደው እርምጃ እናውራ። እርምጃው የተወሰደበት አካሄድ ምን ይመስል ነበር? እርስዎስ እንዴት ያዩታል? ተቀብለውታል? አቶ በረከት:- መሰረተቢስ እርምጃ …

Share this post

One thought on “የብአዴን እግድ መሠረተቢስ እርምጃ ነው ሲሉ አቶ በረከት ስምኦን አማረሩ!

 1. ብአዴን…”በመቀጣጠል ላይ ያለውን ክልላዊና ሃገራዊ ለውጥ ለመጠበቅ፣ መሰረቱን ለማስፋትና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ እንዲቻል ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሕጋዊ የለውጥ እርምጃዎች በተከታታይ ይወሰዳሉ፡፡”
  ** በረከት ስሞዖን :- መሰረተቢስ እርምጃ ነው። ይሄ የሚጠበቅ ነገር ነበር። ይሄ ገና የመጀመርያቸው ነው (just a tip of the iceberg)። ወደፊት ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ይመጣሉ ብዬ እገምታለሁ።እንደ እኔ አስተሳሰብ ይሄ እርምጃ የመጣው አንደኛ ምክትል ጠ/ሚሩን በቅርቡ በተካሄደው የመተካካት ወቅት አለመደገፌ፣ በአቋሜ የማልደራደር ስለሆነ እና ፊት ለፊት ስለምናገር እንዲሁም የማጥራት አካሄድ (cleansing move) ነው። ምክንያቱም በረከት ከተለየ አካባቢ የመጣ ነው ስለሚባል ነው። እርግጥ ቤተሰቦቼ የኤርትራ ስር መሰረት ቢኖራቸውም እኔ ተወልጄ ያደግኩት ጎንደር ነው።”
  … ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል! አማራ በሄደበት ይታረዳል! ይፈናቀላል!ይቃጠላል!ይበለታል! ፱ሚሊየን አማራ ተወልዶ ባደገበት እንኳን የማዕከላዊ ኮሚቴ አመራርነት ቀርቶ ወካይ የሌለው መጤ ሰፋሪ ይባላል..ኤርትራዊ በትውልድ አማራዊ !?
  — መለስ ዜናዊ ” በሽግግሩ ውስጥ አማራ የተወከለው “አመለካከቱን በሚያንፀባርቁ” የግድ የዚያ ብሔር ያልሆኑ እንደሆኑ አውቀን ነው”
  ብአዴን…”ቀደም ሲል ሲመራበት የነበረው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ የህዝቡንና የአባላቱን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ግለጽ በሆነ ተሳትፎ እንዲሻሻል ይደረጋል፡፡ በዚህ ረገድ የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት የድርጅታችን አባላት ጥያቄ እስከሆነ ድረስ የድርጅቱን ስያሜ ጨምሮ ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮችም በአግባቡ እየተፈተሹ ሥርዓቱን በጠበቀ መንገድ ማሻሻያ ሊደረግባቸው ይችላል።”
  ***በረከት.. አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ከእኔ ግለ- አስተሳሰብ ጋር አብሮ ስላማይሄድ አልቀጥልም። I’m thinking of coping with it Lidetu’s style (የልደቱን ስታይል ለመከተል እያሰብኩ ነው)።አሁን ያለው ሁናቴ ፖለቲካን fair በሆነ መልኩ ለማካሄድ ያመቻል ብዬ አላምንም።”
  ብአዴን..”ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ ማሻሻያ ሳይደረግበቸው የዘለቁት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎቻችን ውስጥ አንዳንዶቹ አገራችን ዛሬ ከደረሰችበት የዲሞክራሲ እድገት ደረጃ ጋር ተጣጥመው መሄድ አለባቸው የሚለውን የህዝብ አስተያየትና ጥያቄ ብአዴን በበጎ ጎኑ ይመለከተዋል፡፡

  ጠ/ሚሩ ሹመት ሊሰጥዎ አስበዋል እንበል። ሹመቱን ይቀበላሉ ወይስ በተቃራኒው?
  አቶ በረከት:- በፍፁም! የእስካሁኑ ይበቃኛል።
  — የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች “(የልደቱን ስታይል ለመከተል እያሰብኩ ነው)። ልደቱ በተጣደበት ሁሉ ሲያማስል አንድ ነገር አላበሰለም። ጭራሽም ፓርቲ ሰርቶ ካምፍረስ ወደ ⶃተኛ አማራጭ እያመሰገኑ እያወደሱ መለጠፍንም ቢሆን አብይ አህመድ ጩኸታቸውን ቀምቶ ማስጮህ ጅምሯል…እንግዲህ በየድግሱ እየቀረቡ የፖልቲካ ተንታኝና በታኝ ልደቱ በረከትና ጀዋር የአየር በአይር ፓርቲ ሊያቋቁሙ ይሆን?
  ብአዴን “በዜጎች ለይ የተፈጸመን ማንኛውንም ኀላፊነት የጎደለው ኢ-ሕገ መንግስታዊ ተግባር እያወገዝን በእንዲህ አይነት ድርጊት ውስጥ ገብቶ የተገኘ ማንኛውም ቡድን፣ የመንግስት ባለስልጣንና ግለሰብ የሃገሪቱ ህግ በሚፈቅደው አኳኋን ለህግ ቀርቦ ተጠያቂ እንዲሆን በጽናት እንታገላለን፡፡”
  — የቀድሞው ጠ/ሚር ታምራት ላይኔ ባለቤት እርስዎ ላይ ወቀሳ ሰንዝረዋል። እርሳቸው በመታሰራቸው በእርግጥ ደስተኛ ነበሩ? ከሆነስ ለምን?
  አቶ በረከት:- ታምራት ላይኔ ጉዳይ በፍርድ ቤት ተወስኖ ከዛ ደሞ በህግ መሰረት ተፈቷል። ፲፪ ዓመት ትምህርት ካላስተማረው እኔ ምንም ማረግ አልችልም። እስር ላይ የቆየው ባላደረገው ነገር አይደለም። ማንም ጣቱን ወደ እኔ አሁን ላይ ቢቀስር ለእኔ ምንም ማለት አይደለም።
  ጠ/ሚ አብይ አህመድን ይህ የይቅርታ እና ምህረት ግዜ ወደፊትም መቀጠል አለበት። ዋናው ግን ይህ ሀገር sensetive ስለሆነ የ balance ስራ ሁሌ መሰራት አለበት።”
  — በእርግጥ አቶ በረከት ስሞዖን የለውጥ ደጋፊ ናቸው? ወይስ ያለፈ ጥፋታቸው በይቅርታ በመታለፉ ደግፊ/ተለጣፊ? በእርግጥ ፖለቲካ/ሥልጣን ካልፈለጉ አማራ ካልፈለጋቸው በኤርትራ ማሊያ ሊሰለፉ ይሆን?
  ብአዴን ” አሁን ከተደረሰበት የትግል መድረክና ከለውጡ እንቅስቃሴ ጋር አብረው መጓዝ በተሳናቸውና ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት ባልቻሉ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ድርጅቱ ራሱን የማጥራት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡”
  በረከት “ይሄ ገና የመጀመርያቸው ነው (just a tip of the iceberg)።” ሲሉ አማራ ክልልና ብአዴን ውስጥ አርቀው የቀበሩት መርዝ ሰንኮፉ ይመነገላል ብለው አውቀውታል!? ወይስ መኖሩን መጠቆማቸው ነው?
  ብአዴን “የጥረት ኮርፖሬት እና የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የተባሉት የልማት ድርጅቶች የክልሉ ህዝብ ሃብት እነደመሆናቸው መጠን የላቀ ልማት ማረጋገጥ በሚችሉበት አኳኋን መመራት ስላለባቸው ተጠሪነታቸውም ለክልሉ መንግስት እንዲሆን የፖለቲካ ውሳኔ ተወስኗል፡፡
  [በረከት በመወለድ ያገኘው አማራነትና ተስፋዬ ግብረእባብ በሞጋሳ ያገኘው ኦሮሞነት ገዳ አሳዘነኝ]….
  እግዳው መሰረተ ቢስ ሳይሆን ጥልቅ መሠረት ያለው ሥርተከል ለውጥ ነው በለው!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.