የቦሌ ቄሮዎች ነን የሚሉ ወጣቶች ሜንጫና ገጀራ በመያዝ ድብደባና ማስፈራሪያ ፈጸሙ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/101596

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ሚካኤል አከባቢ የቦሌ ቄሮዎች ነን በሚሉ በቁጥር 200 የሚደርሱ ወጣቶች እና በአከባቢው ወጣቶች መካከል ከትላንት ጀምሮ አለመግባባት ነበር፡፡ ነገሩ እየተባባሰ ሄዶ ዛሬ ወደ ኣላስፈላጊ ግጭት አምርቷል፡፡

 

ራሳቸውን የቦሌ ቄሮዎች በማለት ከሚገልፁት ወጣቶች መካከል አንዳንዶቹ የስለት መሳሪዎችን (ሜንጫና ገጀራ) በመያዝ በአከባቢው ወጣቶች ላይ ድብደባና ማስፈራሪያ ፈፅመዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ፖሊስ በአከባቢው ደርሶ ወጣቶቹን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ታውቋል::

 

የአከባቢው ወጣቶች ከቄሮዎች ጋር ግጭት ውስጥ ከመግባት አልፈው በአከባቢው በሚገኘው የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ህንፃና (ሰራተኞች) ላይ ጥቃት ፈፅመዋል፡፡ (ስዩም ተሾመ) 

Share this post

One thought on “የቦሌ ቄሮዎች ነን የሚሉ ወጣቶች ሜንጫና ገጀራ በመያዝ ድብደባና ማስፈራሪያ ፈጸሙ

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.