የተለያዩ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች ለ1 ሺህ 494ኛው የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%88%E1%8B%AB%E1%8B%A9-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8E%E1%89%BD-%E1%88%AD%E1%8B%95%E1%88%B0-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8B%B3%E1%8B%B5%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%88%881-%E1%88%BA/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች 1 ሺህ 494ኛው የመውሊድ በዓልን አስመልክተው ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

በዚህ መሰረትም የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የደቡብ ክልል ምልክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብርም በመተሳሰብ፣ የተቸገሩ ወገኖቹን በመርዳት እና ስለ ሰላምና አንድነት በመፀለይ መሆን እንደሚገባው ርዕሰ መስተዳድሮቹ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት 1 ሺህ 494ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሠዓወ) የልደት በዓልን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.