የተመድ የየመን የሰብአዊ ርዳታ ፕሮግራም መዘጋት ሰባዓዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ተገለፀ

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%98%E1%8B%B5-%E1%8B%A8%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%89%A5%E1%8A%A0%E1%8B%8A-%E1%88%AD%E1%8B%B3%E1%89%B3-%E1%8D%95%E1%88%AE%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%88%9D/

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 16፣ 2011(ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የየመን የሰብዓዊ ርዳታ ፕሮግራም መዘጋት ሰባዓዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ተገለፀ፡፡

በሀገሪቱ 12 ሚሊየን ዜጎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳት ድጋፍ ሲደረግ መቆየቱ ተነግሯል፡፡

ከተረጅዎቹ መካከል 2ነጥብ 5 ያህሉ ህፃናት ሲሆኑ÷ አብዛኛዎቹ በርሃብ የተጎዱ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የጤና ክትትል የሚያደረጉ እናቶችን ጨምሮ 9 ሚሊየን ያህል ዜጎች ከጤና አገልግሎት ውጭ ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡

ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ 5 ሚለየን ያህል ዜጎች ለንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር የሚጋለጡ እና በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መጠለያ አልባ ይሆናሉ ተብሎ ተሰግቷል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የሰባዊ እርዳታ ፕሮግራም ለመዝጋት የወሰነው የዜጎች ርዳታ በፍጹም ለጦርነት አገልግሎት አይውልም ከሚል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም በየመን ከነበሩት 36 ርዳታ ማስተባባሪያዎች በያዝነው የአውሮፓዊያኑ ዓመት አገልግሎት የሚሰጡት ሶስቱ ብቻ ይሆናሉ ነው የተባለው፡፡

ባለፉት ሳምንታትም አብዛኞቹ የተዘጉ ሲሆን÷ የከፋ ችግር ላይ ለሚሆኑ ዜጎች ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል አንድ ትልቅ ፕሮጀክት ተግባራዊ በማድረግ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት 22 ያህል የእርዳታ ምዕከላት እንደሚዘጉም ነው ዘገባው የሚስረዳው፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን አፍሪካ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.