የተማሩ የኦሮሞ ምሁራን ማደናቆር ወይንስ መደንቆር? እና የዶክተር መረራ የቁመትልክ ስልጣን

Source: https://mereja.com/amharic/v2/200470

Image may contain: Mengistu Musie, smilingMengistu Musie
የተማሩ የኦሮሞ ምሁራንማደናቆር ወይንስ መደንቆር? እና የዶክተር መረራ የቁመትልክ ስልጣን
በመንግስቱ ሙሴ
ኢትዮጵያዊው ማነው? የሚል ጽሁፍ በ 1960 ወቹ መጀመሪያ ያቀረቡት የያኔ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በየካቲት አብዮት ማግስት መጀመሪያ መኢሶን ኋላ ኦነግ ሆነው ዘመናቸውን ኖረዋል። ያነን መጣጥፍ ለተማሪው ያቀረቡት የያኔ ተማሪ ዘመን እድሜአቸውን ኢትዮጵያዊነት የተሰማቸው እንዳልሆኑ መገመት ከባድ አይደለም። የኔ የሁልግዜ ጥያቄ ይህ ነው። የኔ እና መሰል ዘመዶች አያት ቅድም አያቶች የሀገር ዳር ድንበር ሲደፈር ጭብጦ ይዘው ሲዘምቱ እና ሲቆስሉ ሢሞቱ እንደኖሩ ሲነገረኝ አድጌአለሁ። ባንዳነት ክህደት እና ሀገርን አሳልፎ መስጠት የተጸየፉት ዘመዶቸ በቁመቴ ልክ ስልጣን ሳይሉ እንዳለፉም አውቃለሁ። አያቴ ከሽሬ መልስ በመርዝጭስ ያጋጠማቸውን አይነስውርነት በጸጋ ተቀብለው እንዳለፉም ተደጋግሞ ተነግሮኛል። ለሀገር በተደረገው ሁሉ ዋጋ ከፈላ አይደለም የቁመት ያህል ስልጣን ለደከሞ ለቆሰሉበት መዳሊያ ሳያገኙ የበላይ ተከታይ ተብለው ያለፉ ዘመዶቸን ሳስታውስ ስለሀገር የከፈሉትን ዋጋ ጠያቂወች እንዳልነበሩ/ይከፈለን እንዳላሉ በይበልጥም ማንም ምንም ይበል እነርሱ ግን በሰሩት ስራ ከማንም ምርቃት ወይንም ሽልማት ሳይጠብቁ በኩራት እንዳለፉ የሚገባኝ አሁን ነው።
የአጭሯ ታሪክ መነሻየ የዶክተር መረራ በቁመታችን ልክ ስልጣን እና የብዙ የእርሳቸው መሰሎች ሁሉንም ጠቅለው ቢይዙ አሁንም ጭቁን ነን ከሚለው አስተሳሰብ ነጻ ሊሆኑ እንደማይችሉ ዘመን አስቆጣሪ አስተሳሰብ መሆኑን ነው። ከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከቅርቡ ግዜ እንኳን ብንጀምር ከጎበና ዳጨ እስከ ኀብተጊወርጊስ ዲነግዴ፣ ጄኔራል ተፈሪ ባንቲ እስከ መንግስቱ ኃይለማሪያም የሀገሪቱ ጫፍ ስልጣን በማን እጅ ነበር አሁንስ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.