የታክሲዎችን ስምሪትና የታሪፍ አከፋፈል የሚቆጣጠር ነፃ የስልክ ጥሪና የሞባይል መተግበሪያ ሊተገበር እንደሆነ ተገለጸ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/145835

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን ስምሪትና የታሪፍ አከፋፈል የሚቆጣጠር ነፃ የስልክ ጥሪና የሞባይል መተግበሪያ ሊተገበር እንደሆነ ተገለጸ
EBC : በአዲስ አበባ የሚኒባስ ታክሲዎችን ስምሪትና ተገቢ ያልሆነ የታሪፍ ክፍያዎችን በዘመናዊ መንገድ ለመቆጣጠር ነፃ የስልክ ጥሪና የሞባይል መተግበሪያ በቅርቡ ጥቅም ላይ ሊያውል መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

አዲሱ አሰራርም በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ከማቃለል ባለፈ ሚኒባስ ታክሲዎች በተገቢው መንገድ ለከተማው ህዝብ አገልግሎት መስጠታቸውን ለመከታተል እንደሚረዳ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ በተለይ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ችግር እያለ አንዳንድ የሚኒባስ ባለታክሲዎች በተለይ በምሽት አንዳንዴም ቀን ላይ መንግስት ካስቀመጠላቸው መስመር ውጪና ከታሪፍ በላይ ራሳቸው በሚወስኑት ዋጋ አገልግሎት እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡
ይህም ችግር የተከሰተው በባለታክሲዎቹ ህገወጥ ድርጊት ብቻ ሳይሆን በባለስልጣኑ የታክሲዎችን ስምሪት በሚቆጣጠሩ ሰራተኞ ድክመት እንዲሁም የዘርፉ አገልግሎት ቁጥጥር ዘመናዊ አሰራርን ባለመከተሉ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
በመዲናዋ የሚኒባስ ታክሲዎቹን ስምሪት የሚቆጣጠሩ አንዳንድ ሰራተኞች ታክሲዎች በተመደቡብት ቦታ በየዕለቱ መገኘታቸውን ክትትል ሲያደርጉ ከባለታክሲዎቹ ጋር በመግባባት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያለመወጣት ችግር እንዳለም አንስተዋል አቶ በድሉ፡፡
ይህንንም ችግር ለመፍታት ሰራተኞቹን በአንድ አካባቢ ብቻ ሳይሆን በዙር በተለያዩ ቦታዎች እንዲሰማሩ በማድረግ ተገቢውን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና ችግሩ እንዲፈታ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከታሪፍ በላይ በሚጭኑና ያለመስመራቸው በሚሰሩ የሚኒባስ ባለታክሲዎች ላይ በግብረ ኃይል ደረጃ እርምጃ መወሰድ መጀመሩንም ምክትል ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል፡፡
በዚህም በባለፈው አንድ ወር ውስጥ 927 ባለታክሲዎች ላይ ክስ መመስረቱን ተናግረዋል፡፡
ባለታክሲዎች ከታሪፍ በላይ እንዳይጭኑ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.