የትራፊክ ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ቅጣታቸውን ባሉበት ሆነው እንዲከፍሉ የሚያስችል አሰራር ሊዘረጋ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/04/%E1%8B%A8%E1%89%B5%E1%88%AB%E1%8D%8A%E1%8A%AD-%E1%8B%B0%E1%8A%95%E1%89%A5-%E1%8B%A8%E1%89%B0%E1%88%8B%E1%88%88%E1%8D%89-%E1%8A%A0%E1%88%BD%E1%8A%A8%E1%88%AD%E1%8A%AB%E1%88%AA%E1%8B%8E%E1%89%BD/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትራፊክ ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ቅጣታቸውን ባሉበት ሆነው እንዲከፍሉ የሚያስችል አሰራር ሊዘረጋ መሆኑን የአዲስ አበባ የመንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ የመንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ታመነ በሌ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ አጄንሲው አሁን ላይ እየዘረጋ ያለው አሰራር ዘመናዊና ቀልጣፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሰራሩ የደንብ ጥሰት የሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ባሉበት ሆነው ቅጣታቸውን እንዲከፍሉ የሚያያስችል መሆኑንም ነው የገለጹት።

እንደ አቶ ታመነ ገለፃ አሰራሩ የቅጣት ስርዓቱን ቀልጣፋ እንዲሆን ከማድረጉም በተጨማሪ አደጋዎች ሲከሰቱ በፍጥነት ምላሽ እንዲሰጥ በማድረግ ህይወትን ለማትረፍ የሚያግዝ ነው።

ተቆጣጣሪ የትራፈክ ፖሊሶች በሚይዟቸው ታብሌቶች አሽከርካሪዎቹ ያጠፉትን ጥፋት በመመዝገብ ቅጣታቸውን ወዲያውኑ ባሉበት ሆነው እንዲከፍሉ የሚስችል ነው ብለዋል።

ለዚህ አገልግሎት የሚውሉ 100 ታብሌቶች ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ለማከፋፋል መዘጋጀቱን ጠቅሰው፥ አዲሱን አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም አስረድተዋል።

በዙፋን ካሳሁን

Share this post

One thought on “የትራፊክ ደንብ የተላለፉ አሽከርካሪዎች ቅጣታቸውን ባሉበት ሆነው እንዲከፍሉ የሚያስችል አሰራር ሊዘረጋ ነው

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.