የትዊተር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጃክ ፓትሪክ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%89%B5%E1%8B%8A%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8B%8B%E1%8A%93-%E1%88%B5%E1%88%AB-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%8D%88%E1%8D%83%E1%88%9A-%E1%8C%83%E1%8A%AD-%E1%8D%93%E1%89%B5%E1%88%AA%E1%8A%AD-%E1%8A%A2/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትዊተር ዋና ስራ አስፈፃሚ ጃክ ፓትሪክ ዶርሴይ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ ሀገራት ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ እና ጋና የሚደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚው ለአንድ ወር የሚቆየውን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በትናትናው ዕለት በናይጀሪያ ሌጎስ ጀምረዋል፡፡

ጃክ ፓትሪክ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከቴክኖሎጂ ንግስቷ ቤተልሄም ደሴ እና የአፍሪካ ቴክ ኔክስት አንዱ መስራች ከሆነው ኖኤል ዳንኤል ጋር ውይይቱ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም ዋና ስራ አስፈፃሚው ከሌሎቸ በርካታ ስራ ፈጣሪዎች ጋር ሰፊ ጊዜን እንደሚያሳልፉ ነው የተነገረው፡፡

የትዊተር ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ጃክ ፓትሪክ ዶርሴይ አሜሪካ የኮሙፒውተር ፕሮግራመር እና ኢንተርኔት ስራ ፈጣሪ እንዲሁም ስኩዌር የተባለው የሞባይል የክፍያ ኩባንያ ስራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.