የትግራይ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ያካሂዳል

Source: https://fanabc.com/2019/03/%E1%8B%A8%E1%89%B5%E1%8C%8D%E1%88%AB%E1%8B%AD-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%88%AD-%E1%89%A4%E1%89%B5-%E1%88%98%E1%8B%B0%E1%89%A0%E1%8A%9B-%E1%8C%89%E1%89%A3%E1%8A%A4%E1%8B%8D/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ክልል ምክር ቤት 5ኛ የስራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤውን ለሁለት ቀናት እንደሚያካሂድ ነው የተመለከተው።

በእነዚህ ሁለት ቀናትም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

በተለይም የግብርና ስራ፣ የመጠጥና መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች እንዲሁም የመንገዶች ግንባታ አፈፃፀም ይገመግማል።

በተጨማሪም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የተጠያቂነት ስርዓት ለመወሰን የወጣን ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ያስታወቀው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.