የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ወደ አማራ ክልል አልክም ማለቱ እያነጋገረ ነው።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/158590
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/D93AA6A2_2_dwdownload.mp3

DW – የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምሕርት ቢሮ የአንደኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን የግጭት ስጋት አለብኝ ወደሚለው ወደ አማራ ክልል አልክም ማለቱ እያነጋገረ ነው። ውሳኔውን የደገፉ እርምጃው ተገቢ ነው ሲሉ የተቃወሙት ደግሞ የተማሪዎችን መብት የሚጋፋ እና ለፀብም የሚያነሳሳ ሲሉ ተችተውታል። የአማራ ክልልም የአጸፋ እርምጃ ከመውሰድ እንዲቆጠብ ያሳሰቡም አሉ። ዶቼቬለ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ የፌደራል ትምህርት ሚኒስትርና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር የሥራ ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ቢጠይቅም «እየተወያየንበት ነው» ሲሉ መልሰዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.