የትግራይ ፖለቲከኞች፤ ህዝቡን 360 ድግሪ ተከበሃል እያሉ እያስጨነቁት ነው – አቶ ገብሩ አስራት

Source: https://mereja.com/amharic/v2/83827

አዲስ አድማስ
• ያልተገባ ቅስቀሳ በማድረግ ህዝብን ወደ ጦርነት መግፋት ፈጽሞ ሊፈቀድ አይገባውም
• ሀገርን በእልህ ለማፍረስ ከመጣደፍ፣ መንግስት በሆደ ሰፊነት መደራደር አለበት
• የትግራይ ፖለቲከኞች፤ ህዝቡን 360 ድግሪ ተከበሃል እያሉ እያስጨነቁት ነው
የህወሓት መሥራችና የ”አረና” አመራር የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት፤ በወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር ተከታዩን ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ እነሆ፡-

የትግራይ ክልል በሠብአዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩት የቀድሞ የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋን ለህግ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑ ተነግሯል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
በኢትዮጵያ ህግ መከበር እንዳለበት ጥፋተኛም ሊጠየቅ እንደሚገባው አምናለሁ፡፡ ያም ሆኖ ግን ህግ ሲከበር በተለይ አሁን ያለው የሙስና፣ የሌብነት ወይም የሰብአዊ መብት ጥሰት በግለሰቦች ደረጃ ብቻ የሚታይ አይደለም፡፡ ጉዳዩ የስርአት ነው፡፡ ሀገራዊ ነው፡፡ ሠፊ ፖለቲካዊ አንደምታ ያለው ጉዳይ ሆኗል፡፡ እንግዲህ እንደምናውቀው፣ ከአሁን በፊት በግለሰቦች ደረጃ ይታይ የነበረ ነው፡፡ አሁን ግን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታይ ነው፡፡ ይሄ ሲሆን የትግራይ ክልል የሚያቀርባቸው ክርክሮች አሉ፡፡ ክርክሮቹ ትክክል ናቸው አይደሉም የሚለውን ወደ ጐን ትተን፣ አሁን የሚደረገውን በሌብነት የተጠረጠሩትን የማሠርና የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ ሰዎችን የመቆጣጠር ጉዳይ፣ ከወንጀል አልፎ ፖለቲካዊ ይዘት አለው፡፡ ይሄ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ትልቁ ሚስጥር ይሄ ነው፡፡
ይህን ለማለት ያበቃዎት ምክንያት ምንድን ነው?
እንግዲህ ሁላችንም እንደምናውቀው፣ ባለፉት 27 አመታት፣ የኢህአዴግ ባለስልጣን ሆኖ ሙስና ያልፈፀመ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት ያልፈፀመ የለም። በእኛም በኩል

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.