የትግሬ ወያኔዎች በዘረፉት 55. 7 ሚሊዮን ብር የህወሃትን ታሪክ እየጻፉ እንደሆነ ታወቀ

Source: http://welkait.com/?p=7744

በነገራችን ላይ የትግሬ ወያኔዎች የህወሃት ታሪክ የሚሉትን መጽሃፍ ለመጻፍ 55 ነጥብ 7  ሚሊዮን ብር ሲያወጡ 10 ብር ብቻ እንደወጣበት የሚገመተው የአማርኛ ተናጋሪ የህወሃት ክንፍ የሆነው ብአዴን “የኢህዴን/ብአዴን ታሪክ 1973-2008 ዓ.ም” በሚለውን የጻፈውን መጽሃፍ ከሚከተለው ሊንክ ላይ ዳውንሎድ አድርጎ ማንበብ ይቻላል። (የኢህዴን/ብአዴን ታሪክ 1973-2008 ዓ.ም, pdf)

ማሳሰቢያ፡- የሚከተለው ጽሁፍ ከትግሬ ወያኔ ዌብሳቶች ውስጥ አንዱ በሆነው አይጋ ፎረም ከሚባለው ዊብሳት የተወሰደ ነው።

****
የትግራይ ሕዝብና የህወሓት የትጥቅ ትግል ታሪክ በመጽሐፍ መልክ ሊዘጋጅ ነው መቀሌ ሚያዝያ 12/2009 የትግራይ ሕዝብና የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የትጥቅ ትግል ታሪክ በመጻህፍ መልክ ለማዘጋጀት መረጃ የማሰባሰብ ሥራው 80 በመቶ መጠናቀቁ ተጠቆመ። በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ጽህፈት ቤት የታሪክ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊ አቶ ተክለብርሀን አርአያ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ መጽሀፉ የሚዘጋጀው የክልሉ ህዝብና ህወሓት ያካሄዱት መራራ የትጥቅ ትግል ታሪክ ያለ አንዳች መዛበት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ነው። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የሚዘጋጀው መጽሀፍ በህወሓት የትጥቅ ትግል ታሪክ ሰፊ እውቀት እንዲኖራቸው ለሚሹ ዜጎች እንደ አንድ ማጣቀሻ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ተናግረዋል።

መጽሀፉ በትግረኛ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የሚዘጋጅ ሲሆን፤ ለመጽሐፉ ታሪክ የሚሆን መረጃ ለማሰባሰብ፣ በመጽሐፍ መልክ ለማሳተምና ለሥራ ማስኬጃ 55 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ተመድቧል። ገንዘቡም ከህወሓት አባላት መዋጮ የተገኘ መሆኑን የገለጹት አቶ ተክለብርሀን፣ የህወሓት የትጥቅ ትግል ጉዞና ከህወሓት ጋር የተሰለፉ ድርጅቶች፣ የትግራይ ህዝብ የማያቋርጥ ድጋፍና የተደራራቢ ድሎች ምስጢር እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሥራዎችና ያስገኟቸው ደማቅ ድሎች የሚሉት በመጽሀፉ ከሚዳሰሱ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ዋነኞቹ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በአሁኑ ወቅትም መጽሀፉን ለማዘጋጀት የሚያስችሉ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ይዘት ያላቸው መረጃዎች መሰብሰባቸውንና ለቀጣይ ዓመትም መጽሐፉ ለህትመት ለማብቃት እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል። ላለፈው አንድ ዓመት በተደረገው እንቅስቃሴ መረጃ የማሰባሰብ ሥራው 80 በመቶ መጠናቀቁን አቶ ተክለብርሀን ተናግረዋል። በመጽሀፍ ዝግጅት ሥራው ላይ ታሪክ ሳያዛቡ እውነተኛ የህወሓትና የትግራይ ህዝብን ማንነት በሚያሳይና ሌሎችን በሚያስተምር መልኩ ተገቢ ጥናት አድርገው የሚፅፉ የታሪክ ምሁራንንና ተማራማሪዎች ይሳተፋሉ። መጽሐፉ ታትሞ ለህዝብ ከመሰራጨቱ በፊት በየምዕራፉ በህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ፣ በተለያዩ ምሁራንና የህዝብ ውክልና ባላቸው የክልሉ ተወላጆች እንዲገመገም ይደረጋል።

መጽሀፉን ለማዘጋጀት የሚያስችለውን አብዛኛው መረጃ ለመሰብሰብ አንድ ዓመት መፍጀቱን የገለጹት ደግሞ የታሪክ ረዳት ተመራማሪና መጽሐፉን የሚያዘጋጀው ቡድን መሪ ዶክተር ፀጋይ በርሀ ናቸው። መጽሐፉ ከትጥቅ ትግሉ መነሻ ጀምሮ እስከ ሽግግር መንግስት ድረስ የተሰራውን ታሪክ አካትቶ የሚጻፍ መሆኑን ጠቁመው፣ በአሁኑ ወቅት በሕይወት ያሉና የሌሉ፣ ተቃዋሚ የሆኑም ያልሆኑም በትግል ሂደቱ ወቅት የነበራቸው አዎንታዊ ሚና ሳይሸራረፍ በመጽሐፉ እንደሚቀመጥ አስረድተዋል።

የታሪክ ረዳት ተመራማሪ አቶ አብራሃ አድሃና በበኩላቸው፣ መጽሐፉ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለደራሲያንና ለኪነጥበብ ባለሙያዎች ማጣቀሻ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ጠቁመዋል። በ 2010 ዓ.ም ታትሞ ለስርጭት እንዲበቃም እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት። ለመጽሀፉ መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚደረገው እንቅስቃሴ በወቅቱ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮችና የህዝብ አስተባባሪዎች ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸውን ረዳት ተማራማሪው ተናግረዋል።

Source: http://aigaforum.com/news2017/tigrai-people-and-tplf-struggle.pdf

Share this post

One thought on “የትግሬ ወያኔዎች በዘረፉት 55. 7 ሚሊዮን ብር የህወሃትን ታሪክ እየጻፉ እንደሆነ ታወቀ

Post Comment