የንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ወደ 32.22 የኢትዮጵያ ብር ደርሷል፡፡

Source: https://mereja.com/amharic/v2/184023

በዛሬው የንግድ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ ዶላር ወደ 32.22 የኢትዮጵያ ብር ይመነዘራል። በአንድ ወር ውስጥ ብቻ ከነበረበት 29 ብር አካባቢ ወደ 32.22 ደርሷል፡፡ ይህም ማለት ወደ አስር ፐርሰንት አካባቢ ጨምሯል ማለት ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ገበያው የመሪነቱን ሚና እየተጫወት መሄዱን እና የውጭ ምንዛሬ ገበያው ነጻ ለመሆን እየተንደረደረ ለመሆኑ አንዱ ማሳያ መንገድ ነው፡፡
በአንድ ወቅት ጎረቤት አገር ኬንያ ከፍተኛ የሆነ የዶላር እጥረት ሲያጋጥማት አንድ መላ ዘየደች። የዶላር ገበያውን ነጻ አደረገቸው፡፡
ወዲያው መንግሰት በገበያው ሃይል ላይ የተንተራሰ የውጭ ምንዛሬ ተመን መተገበር ጀመረ፡፡ በዚህ ጊዜ በመንግስት ጡንቻ ስር ሆነው ተፈላጊውን የዶላር ምንጭ ማምጣት ያልቻሉት የገበያ ትስስሮች ነጻ ሆነው በገበያው ላይ መሰረታቸውን ሲጥሉ ቀስ በቀስ በፍላጎቱና በአቅርቦት መካከል ሚዛን መፍጠር ጀመሩ፡፡ በአሁን ወቅት ለኬንያ ኢኮኖሚ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ተፈላጊውን ምርታማነት አያሳጣቸውም፡፡ እንደውም በባንክ ያለውና በጥቁር ገበያው ያለው የምንዛሬ ተመን ተመሳሳይ ነው፡፡

በተቃራኒው ኢትዮጵያ ላይ በውጭ ምንዛሬ እጥረት አያሌ ኢንቨስትመንቶች ሲቆሙና መጨረስ ባለባችው ሰዓት አልቀው ወደ ማምረት አግልገሎት እንዳይገቡ ጋሬጣ ሆኖባቸው ቆይቷል፡፡ በታቀደላቸው የጉዜ ሰሌዳ ስራ አጥነትን ይፈታሉ የተባሉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ሲባክኑ ይስተዋላል።
እንደ አገር የግብርና ምርት ላይ እንደተመሰረተ ምጣኔ ሀብት የዶላር ተመን ጭማሬው እንደ አገር የወጪ ንግድ ገቢያውን፤ ብሎም የንግድ ሚዛኑንና ጠቅላላ የክፍያ ሚዛኑን ሊያንገዳግደው ይችላል። በመሆኑም ለጊዜውም ቢሆን የማክሮ ኢኮኖሞ ኢምባላንስ ሊፈጥር ይችላል። ይሁን እንጂ ችግሩ ጊዜአዊ ነው። መንግሰት ይህን የገበያ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.