የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዎች ታወቁ

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%8B%A8%E1%8A%96%E1%89%A4%E1%88%8D-%E1%88%BD%E1%88%8D%E1%88%9B%E1%89%B5-%E1%89%B0%E1%88%B8%E1%88%8B%E1%88%9A%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%B3%E1%8B%88%E1%89%81/

የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዎች ታወቁ
( ኢሳት ዜና መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ/ም ) ይህ ሽልማት የ25 ዓመቷን ወጣት ወ/ሮ ናዲያ ሙራድን የዓለም የሰላም ኖቤል ሽልማትን በወጣትነቷ ያገኘኝ ሁለተኛዋ እንስት መሆን አስችሏታል። ባለፈው ተመሳሳይ ዓመት የ17 ዓመቷ ፓኪስታኒያዊቷ ወጣት ማላላ ዩሳፊዛይ የ2017 እ.ኤ.አ. ሽልማትን ማግኘቷ ይታወሳል።
የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ተወላጅ የሆኑት የ63 ዓመቱ ዶ/ር ዴኒስ ሙክዌጌ በበኩላቸው ለበርካታ ዓመታት በእርስበእርስ ጦርነት በምትታመሰው አገራቸው በግዳጅ ተደፈሩው ለማኅጸን ሕመም ተጋላጭ የሆኑ ቁጥራቸው ከአስር ሽህ በላይ ለሚሆኑ ጉዳተኛ ዜጎች የህክምና እርዳታ በመስጠት ህይወታቸውን ታድገዋል።
ዶ/ር ዴኒስ ሙክዌጌ ከዚህ በፊትም የተለያዩ አህጉር እና ዓለምአቀፍ ሽልማቶችን ተሸልመዋል። በ2008 እ.ኤ.አ. በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ሽልማትን ጨምሮ በ2009 እ.ኤ.አ. የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማትን ማግኘታቸውን ቢቢሲ አክሎ ዘግቧል።

The post የኖቤል ሽልማት ተሸላሚዎች ታወቁ appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.