የአሊባባ ሊቀመንበር ጃክ ማ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%8A%E1%89%A3%E1%89%A3-%E1%88%8A%E1%89%80%E1%88%98%E1%8A%95%E1%89%A0%E1%88%AD-%E1%8C%83%E1%8A%AD-%E1%88%9B-%E1%88%88%E1%8B%AD%E1%8D%8B%E1%8B%8A-%E1%8B%A8%E1%88%B5%E1%88%AB/

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሊባባ ሊቀመንበር ጃክ ማ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ።

ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ሲገቡም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቻይና ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከጃክ ማ ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በጉብኝቱ ወቅት፥ አሊባባ ኩባንያ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት መዋዕለ ንዋዩን እንዲያፈስ ግብዣ አቅርበዋል።

በተለይም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስራ ፈላጊ ወጣት በመሆኑ አሊባባ ኩባንያ በኢትዮጵያ ቢሰማራ ውጤታማ እንደሚሆንም ነበር ያስታወቁት።

በዚሁ ወቅት የአሊባባ ሊቀመንበር ጃክ ማ በገቡት ቃል መሰረት ነው አሁን ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት።

 

በአልአዛር ታደለ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.