የአማራ ሕዝብ ቀጣይ የትግል እርምጃ ብዬ የማስበው (አቻምየለህ ታምሩ)

Source: https://mereja.com/amharic/v2/83597

 
የአማራ ሕዝብ ቀጣይ የትግል እርምጃ ብዬ የማስበው [የግል አስተያየት]

ብአዴን ስሪቱ ጸረ አማራ ስለሆነ ወደ አማራ ለመቅረብ በሞከረ ቁጥር የበለጠ እየራቀ የሚሄድ ድርጅት ነው። አብን ደግሞ ተወደደም ተጠላም የአማራ የሕልውና አደጋ የወለደው የአማራ ባለጉዳይ ነው። ብአዴን ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ምክትልነትን ነባር ይዞታው አድርጎ ጌቶቹ እየሆኑ ለሚሰየሙ የበላዮቹ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነ ሽንፍላ ነው። ብአዴን የተፈጠረውና ዛሬም ድረስ የሚሰራው የአማራ ያልሆነውን ጸረ አማራ ነገር ሁሉ በአማራ ላይ ለመጫን ነው። ብአዴን የተቋቋመው የአማራ ክልል ያልሆነውን የአማራ ጠላቶች እቅድ የአማራ ክልል ለማድረግ፤ ሕገ መንግሥት የሚሉትን አማራ ያልተሳተፈበትንና ከአማራ አንጻር የተዋቀረውን የፋሽስት ወያኔ የቅሚያና የግድያ ደንብ የአማራም ሕግ ለማድረግ መለስ ዜናዊ መንግሥታዊ ያደረገውን ሰይጣናዊውንና ጸረ አማራውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ መመሪያው አድርጎ የተፈጠረ ነውረኛ ድርጅት ነው።
በአማራ ላይ የተጋረጠው የሕልውና አደጋ የወለዳቸው የአብን ልጆች ቀደም ሲል የሕወሓት እንደራሴል፤ አሁን ደግሞ የኦሕዴድ ጉዳይ አስፈጻሚ ከሆነው ከብአዴን ጋር አብሮ ለመስራት ማሰባቸው ብአዴን የአማራ ውክልና እንዳለው እውቅና እንደመስጠት ይቆጠራል። በኔ እምነት አማራ መታገል ያለበት ከብአዴን ጋር አብሮ ለመስራት ሳይሆን የአማራ ውክልና ሳይኖረው የአማራን ሳይሆን የጌቶቹን ጉዳይ ለማስፈጸም የተሰየመበትን ወንበር ለመንጠቅና ለአማራ ለማድረግ መሆን ይኖርበታል። የጌቶቹ ጉዳይ አስፈጻሚ እንጂ የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነው ብአዴን ከአብን ጋር እንዲሰራ መፍቀድ የአማራ ባለጉዳይ የሆነውን አብንን ተጠግቶ የአማራ ባለጉዳይ ተደርጎ እንዲቆጠር እድል ማመቻቸት ነው፤ አልፎም የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነው ብአዴን መቆሚያ መሬትና ማስቻያ ሜዳ

Share this post

One thought on “የአማራ ሕዝብ ቀጣይ የትግል እርምጃ ብዬ የማስበው (አቻምየለህ ታምሩ)

 1. “ብአዴን የተፈጠረውና ዛሬም ድረስ የሚሰራው የአማራ ያልሆነውን ጸረ አማራ ነገር ሁሉ በአማራ ላይ ለመጫን ነው። ብአዴን የተቋቋመው የአማራ ክልል ያልሆነውን የአማራ ጠላቶች እቅድ የአማራ ክልል ለማድረግ፤ ሕገ መንግሥት የሚሉትን አማራ ያልተሳተፈበትንና ከአማራ አንጻር የተዋቀረውን የፋሽስት ወያኔ የቅሚያና የግድያ ደንብ የአማራም ሕግ ለማድረግ መለስ ዜናዊ መንግሥታዊ ያደረገውን ሰይጣናዊውንና ጸረ አማራውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ መመሪያው አድርጎ የተፈጠረ ነውረኛ ድርጅት ነው።”

  አብን ደግሞ ተወደደም ተጠላም የአማራ የሕልውና አደጋ የወለደው የአማራ ባለጉዳይ ነው።

  አሁን አማራ እየተጠናከረ ባለበት ሁኔታ ነፍስ አልባው ብአዴን ነፍስ ካለው አብን ጋር የሚመሰርተው ኅብረት ከተዳከመበት አፈር ልሶ እንዲሳ የሚያደርግና አማራን የሚያዳክምበት ጉልበት እንዲያገኝ የሚያደርግ ነው።

  ዛሬ አብን ብአዴንን የአማራ ባለጉዳይ አድርጎ ከብአዴን ጋር ከተዋዋለ ነገ በአማራ ጉዳይ ጌቶቹ ብአዴን ይወከል ሲሉ ብአዴን አማራን አይወክልም ብሎ ለመናገር የሚያስችል አመክንዮ ሊኖረው አይችልም።

  *** አብን መደርደር ሳይሆን መደራደርና መገዳደር ያለበት*****
  “ብአዴን በጌቶቹ እንደራሴነት እየገዛ(በሚገዘግዛቸው) አካባቢዎች ሁሉ ነጥቆ በመውሰድ የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነውን ብአዴንን ማቆሚያ ማሳጣት እንጂ ለብአዴን ሕጋዊነት በማላበስ ስር እንዲሰድ እድል ማመቻቸት መሆን የለበትም።”
  በአብን መሪነትና አስተማሪነት ወጣቱን በማደራጀት ” በቁርጠኝነት አማራው በመየንደሩ፣ በየሰፈሩ፣ በየቀበሌውና በየወረዳው የአማራ ባለጉዳይ ያልሆነው፣ የጸረ አማራው ሥርዓት በእንደራሴነት ተሰይሞ ፍዳችንን የሚያራዝመውን ብአዴንን ማቆሚያ እንዲያጣ በማድረግ፤ የየራሱን አካባቢ ሕጋዊነት ከሌለው ከእንደራሴው ብአዴን አገዛዝ ነጥቆ በመውሰድ የባዕድ ምንደኞች በመሆን ተጭኖት የኖረውን ነውረኛ ድርጅት ነቅሎ ጥሎ ራሱን ማስተዳደር በመጀመር ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋራ በጋራና በእኩለት የሚኖርባትን አገር፣ ሕግና ሥርዓት ለመመስረት መደራደር መጀመር አለበት።

  *********************

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.