የአማራ ማህበር በሆላንድ የሽመልስ አብዲሳን ሽልማት በመቃወም ሆላንድ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ኢምበሲ እና ለውጭ ጉዳይ ሚንስተር አቤቱታውን አሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጳጉሜ 5 ቀ…

የአማራ ማህበር በሆላንድ የሽመልስ አብዲሳን ሽልማት በመቃወም ሆላንድ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ኢምበሲ እና ለውጭ ጉዳይ ሚንስተር አቤቱታውን አሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 5 ቀ…

የአማራ ማህበር በሆላንድ የሽመልስ አብዲሳን ሽልማት በመቃወም ሆላንድ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ኢምበሲ እና ለውጭ ጉዳይ ሚንስተር አቤቱታውን አሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ የሰጠውን የእውቅና ሽልማት በመቃወም ሆላንድ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምበሲ እና ለውጭ ጉዳይ ሚንስተር አቤቱታውን አሰምቷል። በአቤቱታውም እንዳለው በጳጉሜ 02/2012 ዓ.ም የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ክልሉ ያሳየውን አንጻራዊ ሰላም በሚመለከት አስተዋጸኦ ለነበራቸው አካላት የእውቅና መርሃ ግብር በባህር ዳር ከተማ አዘጋጅቶ ነበር። ዝግጅቱንም በቴሌቪዥንና በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አውታሮች ተከታትለነዋል፤ ዝግጅቱ ላይ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ለአማራ ክልል ሰላም አስተዋጻኦ ካደረጉ አካላት መካከል ተገኝተው ከአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ነው ያለው ማህበሩ በመግለጫው። የአማራ ማህበር በሆላንድ(አማሆ) አቶ ሽመልስ መሸለማቸውን ከመቃወም አልፎ ግለሰቡ ለህግ መቅረብ ይገባቸዋል የሚል ጽኑ አቋም እንዳለውም ገልጧል። የሁላችንን ልብ ያደማውና ጠባሳው መቼም የማይጠፋው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ሽፋን በማድረግ ከሰኔ 22 ሌሊት እስከ 25 ቀን 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ክልሉን በሃላፊነት በሚመሩት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ቸልተኝነት እና ሃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣታቸው መሆኑ ጋሀድ የወጣ እውነታ ነው ሲል ማህበሩ አስታውቋል። ከዚህም በላይ ግለሰቡ በተለያዩ ጊዜያት ጸብ አጫሪና በተረት ተረት አንድን ህዝብ በሌላው ላይ እንዲነሳ የሚያድርጉ ንግግሮችን በማድረግ ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ቀጥተኛ ተጥያቂም ናቸብሏልው። የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የሆነውን የዜጎችን ሰላምና ደኅንነት የማሰከበር ኃላፊነታቸዉን በአግባቡ ሊወጡ ባለመቻላቸውም ለ200 በላይ አማሮች ሞትና ቁሳዊ ውድመት ከገዳዮች እኩል ሁሉም የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በህግ አግባብ መጠየቅ ነበረባቸው፡፡ ሁሉም በህግ ፊት እኩል ከሆነ ይህ አቶ ሽመልስ ላይም ለሰራ ሲገባው በተቃራኒው በጎ እንደሰሩ ካባ መሸለሙ እጅግ ሰብአዊነት የጎደለው ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል። ከሁሉ ከሁሉ ሽልማቱ የተበረከተው ለአማራ ህዝብ ቆሜአለሁ በሚል አካል መሆኑ ነገሩን የበለጠ አሳዛኝ ያድርገዋል። ከመርሃ ግብሩ አላማ ጋርም ፈጽሞ የማይገናኝና የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ለአማራ ህዝብ ያለውን ንቀትና ደንታ ቢስነት ያሳየበት ነው ብለን አናምናለን። የአማራ ማህበር በሆላንድ: ሀ) አቶ ሽመልስ አብዲሳ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት በስሙ ጠርተው ለተፈፀመው ወንጀል ክልላዊ መንግስታቸውን ወክለው ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠየቁ፤ ለ) መንግሥት የተፈፀመውን የዘር ፍጅት የሚያጣራና የሚመረምር ኮሚሽን አቋቁሞ ወንጀለኞችን ለህግ እንዲያቀርብ፤ ሐ) የኦሮሚያ ክልል በክልሉ ለሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ህዝቦች ሰብአዊና ህገ መንግሥታዊ መብቶቻቸው የሚከበሩበት ዋስትና እንዲሰጥ አማሆ እየጠየቀ፣ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ለአቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚሰጡ ማንኛውም አይነት እውቅና ህዝባችን ቁስል ላይ ስንጥር እንደመስደድ የምንቆጥረውና የማንቀበለው መሆኑን እንገልጻለን በማለት መግለጫውን ቋጭቷል ሲል አዲስ ኤክስፕረስ ሚዲያ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply