የአማራ ብሄራዊ ንቃንቄ- አብን፣  ሕወሃትን የሽብር ቡድን ብሎ፣ በሕግ እንዲታገድ ጠየቀ 

Source: https://mereja.com/amharic/v2/73177


የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) በምእራብና መካከለኛ ጎንደር ዞኖች በቅማንት ስም የተደራጁና በሕወሃት የሚትገዙ ቡድኖች እየፈጠሩ ባሉት ቀውሱ ዙሪያ ማወጣው መግለጫ፣ ሕዝብን እያሸበረ ነው ያለው የኢሕአዴግ አባል ደርጅት የሆነው ሕወሃትን ከሷል።
“በአማራ ሕዝብ በአጠቃላይ፤ በሰሜን ምዕራብ አማራ በተለይ እየደረሰ ላለው የሽብር ድርጊቶች ጠንሳሽ እንዲሁም የሥልጠና፣ የትጥቅና ፋይናንስ ድጋፍ እያደረገ የሚገኘው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር–ሕወኃት ነው” ያለው አብን ” ቡድኑ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በተለይም በአማራ ሕዝብ ላይ በፈፀማቸውና እየፈፀማቸዉ ባሉ የዘር ማጥፋት፣ ዘር ማፅዳት፣ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ከፍተኛ ዘረፋና ውንብድና እንዲሁም በአገርና በሕዝቦች አንድነት ላይ እየፈፀመ ባለው የሽብርና የጥፋት ድርጊቶች መነሻነት በአሸባሪነት ተፈርጆ ከማናቸውም የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች መታገድ እንዳለበት አብን በጽኑ ያምናል። ስለሆነም ሕወኃት ከአገሪቱ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝርዝር ውስጥ እንዲፋቅ አብን እየጠየቀ ከዚህ አሸባሪ ቡድን ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልኩ የሚሰሩ የንግድ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች/የጥፋት ቡድኖች ግንኙነታቸውን እንዲያቋርጡ አብን በአንክሮ ያሳስባል። ከሕወኃት ጋር ግንባር የፈጠሩ ፓርቲዎችም ውሳኔያቸውን እንዲያጤኑ አብን ይጠይቃል” ሲል በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ጠንካራ መግለጫ ነው ያወጣው።
አብን ሕወሃት እንድታገድ ጥሪ ክማቀረቡ በተጨማሪ፣ የአማራ ክልል መንግስትና እሪ ደርጅቱ አዴፓ ፣ በጎንደር ለተፈጠረው ችግር ሃላፊነት መዉሰድ እንዳለበትም አሳስቧል። “የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትና ገዥ ፓርቲ አዴፓ የሕዝባችንን ሰላምና ደኅንነት ከማስጠበቅ አኳያ ኃላፊነቱን በአግባቡ ባለመወጣቱ የተነሳ በሕዝባችን ላይ ለደረሰው ከፍተኛ ጥፋት ኃላፊነቱን መዉሰድ እንዳለንበት ይገለጸው የአብን መግለጫ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥትና ፓርቲ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.