የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፅ/ቤት ኃላፊ ታሰሩ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/133251


የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ በለጠ ካሳ መታሰራቸውን ምንጮች ገልፀዋል። አቶ በለጠ ካሳ ከአብን አባላትና አመራሮች ጋር ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ መኪና ውስጥ በነበሩበት ወቅት ፖሊሶች ከመኪና አስወርደው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮምሽን (3ኛ) እንደወሰዷቸው ተገልፆአል።
 
የአብን አመራሮችና አባላት በሰኔ 15ቱ ክስተት ሰበብ መታሰራቸውን ተከትሎ የፅ/ቤት ኃላፊው እስሩ በሰበብ የተደረገ መሆኑን ለሚዲያዎች መግለፃቸው ይታወቃል። ከአብን አባላትና አመራሮች በተጨማሪ በሰበብ ስለታሰሩ ሌሎች የአማራ ተወላጆች እንዲፈቱም አብን መጠየቁ ይታወቃል። “አማራ እና እውነት አይታሰርም” የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት የለበሱ የአብን አባላት ታስረው የነበር ሲሆን ሶስቱ የአብንን ደረሰኝ ይዛችኋል ተብለው ዋስትናቸውን እንደተከለከሉ አብን በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።
አሥራት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.