የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

Source: https://fanabc.com/2019/08/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%88%AD%E1%8B%95%E1%88%B0-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%89%B0%E1%8B%B3%E1%8B%B5%E1%88%AD-%E1%8A%A0%E1%89%B6-%E1%89%B0%E1%88%98%E1%88%B5/

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከእንግሊዝ አምባሳደር አላስተር ማክፊል ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ እንግሊዝ ከአማራ ክልል ጋር ከዚህ በፊት በጀመረቻቸው እና በአዳዲስ የልማት እቅዶች በትብብር ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል።

አምባሳደር አላስተር ማክፊል ከዚህ በፊት በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በዘመናዊ የመሬት አያያዝ እና በኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ከክልሉ ጋር በትብብር ለመሥራት መሞከራቸውንም ነው የተናገሩት።

በመገናኛ ብዙኃን ነፃነት ላይ ለመስራት እና ጋዜጠኞችን በስልጠና ለማብቃት ማቀዳቸውንም የእንግሊዙ አምባሳደር አስታውቀዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ራይነር እና ከእንግሊዝ አምባሳደር አላስተር ማክፊል ጋር በቀጣይ የትብብር ተግባራት ዙሪያ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

ከሀገራቱ ጋር በፀጥታ መዋቅር እና በፍትህ ስርዓት ማሻሻያ፣ በፖሊሲ ምርመር እና ስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመሥራት መወያየታቸውንም አቶ ተመስገን ገልጸዋል።

በኢንቨስትመንት አማራጮች ላይም የየሀገራቱን ባለሃብቶች ለመሳብ እና አደጋ ላይ ያሉ ቅርሶችን ለመታደግ በትብብር ለመሥራት መወያየታቸውን ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.