የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከክልሉ የመንግስት ሰራተኞች ጋር እየተወያየ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%88%B2%E1%89%AA%E1%88%8D-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%89%AA%E1%88%B5-%E1%8A%AE%E1%88%9A%E1%88%BD%E1%8A%95-%E1%8A%A8%E1%8A%AD%E1%88%8D/

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከክልሉ የመንግስት ሠራተኞች ጋር በክልል አቀፍ የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ እየተወያየ ነው።

በውይይት መድረኩ ከክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የተወጣጡ 1 ሺህ 500 በላይ የመንግስት ሠራተኞች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉቀን አየሁ፥ በክልሉና ከክልሉ ውጭ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የክልሉን ብሎም የሀሪቱን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግቦች ለማሳካት ጉልህ ሚና ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ባለፈም የህዝቦችን ሰላም፣ ፀጥታና አንድነት ከማስቀጠል ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆኑን ነው ያብራሩት።

በየደረጃው ያለው የመንግስት ሠራተኛ ለውጡ እንዲመጣ የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ አሁን ላይ የሚስተዋሉትን ተግዳሮቶች በመፍታት የዜጎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አንስተዋል።

በአማራ ክልል 372 ሺህ 601 የመንግስት ሰራተኞች የሚገኙ ሲሆን፥ ይህ አሃዝ ከአጠቃላይ ህዝቡ ጋር ሲነፃፀርም አንድ ሠራተኛ ለ59 ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል።

የሲቪል ሰርቪስ ሠራተኛው ሙሉ አቅሙበመጠቀም እና የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባውም አሳስበዋል።

በናትናኤል ትጋቡ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.