የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በአልማ ድጋፍ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ዋሺንግተን ዲሲ ገባ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8A%AD%E1%88%8D%E1%88%8D-%E1%8B%A8%E1%88%A5%E1%88%AB-%E1%8A%83%E1%88%8B%E1%8D%8A%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%88%8D%E1%8B%91%E1%8A%AD-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%88%8D/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ድጋፍ እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ዋሺንግተን ዲሲ ገባ።

በአቶ ዮሐንስ ቧያለው የተመራው የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ዋሺንግተን ዲሲ ሲደርስ፥ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ እና በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች አደረጃጀት ተወካዮች አቀባበል ተደርጎለታል።

የጉዞው ዓላማ በውጭ ሀገራት ከሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች ጋር በአልማ ድጋፍ እና በወቅታዊ የክልሉ እና የሀገሪቱ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ያለመ ነው ተብሏል።

በዚህም በክልሉ ልማት፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በዚህ መሠረት በዋሺንግተን ዲሲ፣ አትላንታ፣ ኦሃዮ፣ ሚኒሶታ፣ ዴንቨር፣ ሲያትል እና ሌሎችም ከተሞች ውይይት ይካሄዳል።

ልዑኩ ከሰሜን አሜሪካ ቆይታው በኋላ ወደ ካናዳ ቶሮንቶ በማምራት ተመሳሳይ ውይይቶችን እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.