የአማራ የምሁራን መማክርት ጉባኤ የመጀመሪያውን ክልል አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው

Source: https://fanabc.com/2019/09/%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%88%AB-%E1%8B%A8%E1%88%9D%E1%88%81%E1%88%AB%E1%8A%95-%E1%88%98%E1%88%9B%E1%8A%AD%E1%88%AD%E1%89%B5-%E1%8C%89%E1%89%A3%E1%8A%A4-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8C%80%E1%88%98/

አዲስ አበባ፣መስከረም 3፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ የምሁራን መማክርት ጉባኤ በመጪው መስከረም 9 እና 10 የመጀመሪያውን ክልል አቀፍ ጉባኤ በባህርዳር እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡

በጉባኤው በሃገሪቱ እና በክልሉ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ጥናቶች ቀርበው ውይይት ይደረግበታል ተብሏል፡፡

የምሁራን መማክር ጉባኤው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ስለ ጉባኤው እና መማክርት ጉባኤው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ጉባኤው፤ የአማራ ህዝብ የፍትህ፣ የነፃነት፣ የእኩልነት፣ የዲሞክራሲ ትግል ለጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የአማራ ክልል ምሁራን መማክርት ጉባኤ በአዋጅ ከተቋቋመ አንድ አመት አስቆጥሯል፡፡

በትምህርት፣ በጤና፣ በፍትህ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በግብርና፣ ተፈጥሮሃብት እና በቴክኖሎጂ ሴክተሮች በመደራጀት ስራዎች መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

የምሁራን መማክርት ጉባኤው የተቋቋመበት ዋና አላማው በክልሉ እና በሃገሪቱ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጎዳዮች ላይ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ትክለኛውን አቅጣጫ ማመላከት ነው ተብሏል፡፡

በሃይማኖት እያሱ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.