የአማራ ጉዳይ | መስፍን ወልደ ማርያም መጋቢት 2010

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/89183

የአማራ ጉዳይ እንቆቅልሽ እየሆነ ነው፤ አማራ ነን እያሉ በስሜት የሚናጡት ሰዎች የሚጽፉትን ያነበበና አልፎ አልፎም አዳማጭ ሲያገኙ የሚናገሩትን የሰማ ከፕሮፌሰር ዓሥራት ጀምሮ የጎሣ ፖሊቲካ ፓርቲ ለማቋቋም የተደረገውን ሙከራ ሁሉ መክሸፉን አልሰሙም፤ አያውቁም፤ መለስ ዜናዊ ከጓደኞቹ ጋር የፈጠረውን ጭራቅ የኩራትና የዳቦ አባታቸው (ዓሥራት ሆዳም ያላቸውን) አድርገው ለመቀበል ዝግጁ ነበሩ፤ ሆኖም ፈልገው ፈልገው እስካሁን አላገኙትም፤ ሆዳሞች ሞልተዋልና […]

Share this post

One thought on “የአማራ ጉዳይ | መስፍን ወልደ ማርያም መጋቢት 2010

 1. ክቡር ሊ/ጠ መስፍን ወልደማርያም ሆይ፤ አማራና ፀሐይ ሁለቱ አንድ ናቸው፡
  ** ፀሐይ ከፕላኔቶች አንዷ ናት ጠዋት ስትወጣ፡ ብርሃንና ሙቀት ትሰጣላች፡ፀሐይ እንደወቅቱ ለሁሉ እኩል ፀጋ ናት፡ወቅት ከመፈራረቅ በስተቀር በሁሉም ሀገራትና፡አህጉር አለች፡ሁሉም ይወዷታል ይጠቀሙባታል፡ ብዙዎች በሰው ሰራሽ ብርሃን ምንጭ ሊተኳት ሞክረዋል አልተቻለም፡ የተፈጥሮ ሕግጋት ሆኖ ጠዋት እንደወጣች ማታ ትጠልቃለች ያ ማለት ግን ፀሐይ የለችም ጠፋች ማለት አይቻልም!። ብትኖርም ነው ወጥታ እስከትጠልቅ ተጠቅመን ተመልሳ እንድትወጣ የምንናፍቃት…..።
  **አማራ ከነገዶች አንዱ ነው በሀገር ምሥረታ፡ ጥበቃና ግንባታ ሁሉ አጥንትና ደሙን ከፍሏል፡ አማራን በተለጣፊና በተመሳሳይ (አመለካከት) አለን በሚሉ መሳይና ተመሳሳይ፡ ሸክላ ለመሥራት ላለፉት ፵፬ ዓመት ተመክሯል፡ ስንጣቃና ሸራፋ ናቸውና ሊሆኑት አልቻሉም፡ ለአማራ መልካም ነገሮች ሁሉ ተራራም ላይ ያሉ፡ ሜዳ ላይ፡ ቆለኛውም ወይናደጋ የተፈጠረ ባሕልና ወጉን ወዶ፡ ተጋብቶ፡ በአበልጅነት ተሳስሮ፡ አማርንኛውን በበለጠ አዳብሮና ተክኖበት ይራቀቅበታል። ኤርትራውያንና የደቡብ ሕዝቦችንም ዓይቶና አድምጦ መደመም ነው። ስለዚህም አማራ የሰፈረበትን መንደር እንደትውልድ ሀገር ሲጠራ ነገዱ አማራ፡ ዜግነትና ማንነቱ ኢትዮጵያዊነት ነው። ዜግነትና ማንነቱን ኢትዮጵያዊነት ላይ መመሥረቱ ጠቅሞታል፡አማራነት ስላላንቆለጳጰሰው ጠልቶታል የለም ማለት አደለም፡፡ ጸሐይ ጠለቀች ማለት የለችም ጠፋች ማለት ሳይሆን ልክ አማራውም አማራነቱ አስፈላጊ ሲሆን ይጠለቃል ይወጣል!! አትፍሩ
  1. አማራ ማለት
  1.2. ከሣቴ ብርሃን ተሰማ
  ‹‹የተመረጠ፣ ነጻነት ያለው ተውልድ፣ … ዐም ሕዝብ፣ ሓራ ሔር የወጣ ጨዋ፣ ነጻነት ያለው ወገን ወይም አሸናፊ፣ ድል ነሺ ዋና አለቃ ማለት ነው፤
  1.3. አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ ‹‹ዐም ሕዝብ፣ ሐራ ነጻ በተገናኝ ነጻ ሕዝብ ገዢነት እንጂ ተገዢነት የማይስማርው ማለት ነው፤ ዐማራነት ዐማራ መሆን ተገርዞ፣ ተጠምቆ፣ ማተብ አስሮ የሚኖር ነው፤
  1.4. አለቃ ዓጽሜ አማራ ከወዴትም አልመጣም ጥሩ የላስቶች ወታደር፣ከየዓይነቱ የተጠራቀመ፣ ኃይለኛ፣ ግፈኛ፣ አድመኛ እውቀት ያለው ያልተማረ ጨካኝ ጭፍራ ነው፤
  1.5. የአባ ዮሐንስ ትግርኛ/አምሐርኛ መዝገበ ቃላት ውስጥ አምሐራ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ነው፤›. የሚል ነው፤
  1.6. ንቡረ እድ ኤርምያስ ዐማራ ማለት ‹‹በነጻነት የመኖርን ጸጋ ከእግዚአብሔር በቃል ኪዳን ላገኘው ከየነገዱና ከየጎሣው በጋብቻ፣ በልደትና በኅብረተሰባዊነት ተዋህዶ አንድ ፍጹም ሙሉ ዘር ለሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰጠ የኅብረ ነገድ ወይም የኅብረ ብሔር አጠቃላይ የባሕርይ መታወቂያ ስያሜ እንጂ የአንድ ጎሣ ስም አይደለም፡፡
  1. 7 አምሃራ ማለት፡ ተራራማ ቦታ (ደጋማ) ቦታ የሚኖር ‘ደገኛ’ ማለት ነው” የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ኮሎኔል መንግስቱ ኅይለማርያም ከሂብሩ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደተረዱት።
  *******************************!
  መስፍን ወልደማርያም አማራ የለም አላሉም። ችግሩ ያለው በሊቀ ጠበብት አስራት ወልደየስ ሐሳብ ተነሳስታችሁም ይሁን እንዲያውም ‘ሆዳም አማራ’ ያላችሁ ሕዝባችሁን በዝምታ ያስበላችሁ አሁን እንዴት ተሰባሰባችሁ የሚል ጥያቄ አዘል የፍርቻና ቁጭት ሓሳብ በስድብ ለውሰው ወርውረዋል።
  *ፍራቻው፤ የመሰባሰቡ ፍጥነትና አደረጃጅቱ አማራ የሚባል አሜሪካ ሀገር ሊፈጠር ነው ያሉት ውሎ አድሮ ቡግ ማለቱ።አብገንግኗቸዋል? አዳሜ ልገንጠል ቢል አማራ ዝም ቢል አርጎት ነው ንካው ቢል!አለቀልን ብለው ብርክ ነው፡
  * ስጋታቸው፤መለስ ዜናዊ አማራ አለ ባይላቸው ለብቻቸው ባይወጡ፡ ሁሉን አቀፍ ትብብር ‘ተሸፋፍኖ’ ቢቀጥል ኢትዮጵያ አትመሰቃቀልም! አማራ ለኢትዮጵያዊነት ደህና ነበር አሁን እራሴን ካለ እግር ያለው ያለ እራስ አይሆንምና አለቀልን ብለው ይሰጋሉ፡ለነገሩ ሞኝ ካመረረ በግ ከበረረ ለዚያውም የመንዝ በግ!? ነጻ ሕዝብ ለሀገሩና ለወገኑ ነጻነት!
  _፟ንቡረ እድ ኤርምያስ ዐማራ ማለት ‹‹በነጻነት የመኖርን ጸጋ ከእግዚአብሔር በቃል ኪዳን ላገኘው ከየነገዱና ከየጎሣው በጋብቻ፣ በልደትና በኅብረተሰባዊነት ተዋህዶ አንድ ፍጹም ሙሉ ዘር ለሆነውየኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰጠ የኅብረ ነገድ ወይም የኅብረ ብሔር አጠቃላይ የባሕርይ መታወቂያ ስያሜ እንጂ የአንድ ጎሣ ስም አይደለም፡፡
  ** ሊ/ጠ መስፍን ወልደማርያም አባታቸው የማርያም ልጅ (ክርስቶስ) ከሆነ ቆላም ተወለዱ ወይና ደጋ እኔም አማራ ነኝ!፡ ክርስቲያን ነኝና ሲሉ የሚያንገዋልሏቸውን ተሳድበውም ይሁን ተማፅነው መሞገታቸው መሰለኝ። ይታዘንላቸዋል እንጂ አይታዘንባቸውም። እራሳቸውን በጂኦግራፊ አማራ ያደረጉ በነገድ አደሉም ከተባሉ እኮ ብዙ ወልደማርያም ከንባታ አለ ኤርትራዊ አለ ትግሬ አለ ኦሮሞም አለ፡ሲዳማ አለ…ጋሞ አለ ጋምቤላና ከፋ አለ።
  ሊ/ጠ መስፍን ብዙ መፅሀፍ የጻፉ፡ ‘የወጡ የወረዱ’ ይልና የጆግራፊ መምህር ይባላሉ፡
  ጆግራፊ(ኅብረት/ተሰብ) ማለት መሬት አቀማመጥ፡ አየር ጸባይ፡ የሕዝብ አሰፋፈርን ቢያጠና ግብረገብ ተምሯል ማለት አደለም። ዘር፡ጎሳ፡ ብሔር፡ነገድ፡ጎጥ፡ሃይማኖት፡ የሚያጠና የራሱ ትምህርት ያለው መሆን አለበት። ሊ/ጠ መስፍን አማራን ጎሳ አድርገው አወርደው ሲፈጠፍጡ ማንን ነገድ ሊያደርጉ ነው? ይህንን ሁሉ መጽሐፍ ካነበቡ አማራ ኖሮ ሥያሜውን ካወቁ በኋላ ሸዋና ወሎ ምን ሊያጠኑ ሄዱ!?
  ** ተስፋ ገብረስላሴ ዘብሔረ ቡልጋ አለ ማለት የተወለድኩት ቡልጋ የምትባል ‘የበልግ ሀገር’ ነው ማለቱ እንጂ ፡ አማራ አደለሁም ከኢትዮጵያ ውጭ ሀገር አለኝ ማለታቸው እንዳልሆነ እንማር! “እውቀት ብርሃን ነው”።
  ** “ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ሦስት ሊቃውንት እንደሚያስረዱት አማራ የአንድ ጎሣ ስም አይደለም አማርኛ ቋንቋ የአማራ የሚባል ጎሣ ነው:: በሌላ ጊዜ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ እንሞክራለን፡፡
  -“የአማራ ጉዳይ እንቆቅልሽ እየሆነ ነው” ሸዋ ውስጥ መርሃቤቴ፡ ደብረብርሃን ጠራ፡ ምንጃር፡ አሳግርት፡ ሰላ ድንጋይ ፡ይፋት፡ መንዝ፡ተጉለት ቡልጋ በወንዝና ተራራ (በወረዳና አውራጃ) ስለተካለለ ጎሳ እንጂ ከአማራ ውጭ የተለያየ ነገድ አደለም። ሊ/ጠ መስፍን ወ/ማርያም ከቅድመ አያታቸው ጀመረው የዘር ሀረጋቸውን በብሔር፡ነገድ፡ጎሳ፡ዘውግ በምሳሌነት ያስረዱን? በእርግጠኝነት አይችሉም! አያውቁትም! ይፈራሉ! ያፍራሉ! አማራና አማርኛ ለመኖሩ ሌሎች ደገኞች ምን አሉ? “አንዳችን ለሁላችንም፡ ሁላችንም ለአንዳችን” ለአንድ አማራ ድርጅት፤
  ከደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ህብረት የተሰጠ የድጋፈ መግለጫ።
  “የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያን በመገንባቱና በመጠበቁ ተግባር እንደሌሎቹ ህዝቦች ሁሉ የጎላ ታሪካዊ ድርሻ አለው። በመሆኑም አሁን ያለዉ ትውልድ በመደራጀት የራሱን ጠንካራ ሥራ በመስራት አገራዊ አደራና ታሪካዊ ሀላፊነቱን በብቃት መወጣት አለበት። በዚህም መሰረት የአማራው ሕዝብ በሚገባዉ መጠን ድርጅታዊ አቅም ፈጥሮ ራሱን ከጥቃት መከላከል ስለሚኖርበት ከሁሉም የሃገሪቱ ህዝቦች ጋራ በመሆን ኢትዮጵያን ከወያኔ አደገኛ የጥፋት ተልእኮ ለመግታት እንዲሁም ሀገሪቱን ከመፈራረሰ ለመታደግ እና ወደፊት የሚፈጠረዉን ዴሞክራሳያዊ ስርዓት ለመመስረት ይቻል ዘንድ “አንድ አማራ” ድርጅት የአማራዉን ህዝብ የማስተባበርና የማታገል ሚና የመጫወት ትልቅ አስተዋጽዖ ማበርከት እንደሚችል ሙሉ እምነት አለን።”
  *አማራ ነበር! አለ! ይኖራልም ! አጥፊዎቹ አይኖሩም!አማራነትና ኢትዮጵያዊነት ድርና ማግ ብሔሮች ጥለት ናቸው።

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.