የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዶናልድ ትራምፕ የጉዞ እገዳ ሙሉ በሙሉ እንዲሰራ ፈቀደ

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/39852

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

በአሁኑ ሰዓት በምትፈጽመው ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የአለምን አይን እና ጆሮ የሳበችው ሰሜን አፍሪካዊቷ ሊብያ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት የጉዞ እገዳ ውስጥ እንድትካተት የሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት  አፅድቋል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጉዞ እገዳጋው ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ተቃውሞ እየደረሰባቸው ቢገኝም በስድስት የሙስሊም ቁጥር በሚበዛባቸው ሀገራት ዜጎች ላይ እገዳ ጥለዋል፡፡ ሊቢያን ጨምሮ እገዳው የተጣለባቸው ሀገራት ኢራን፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ቻድ፣ እና ሶማሊያ ናቸው፡፡

ፍርድ ቤቱ ፱ ዳኞች ያሉት ሲሆን ከእነዚህ መካከል ሁለቱ ዳኞች የአሁኑን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዉሳኔ ውድቅ በማድረግ አወዛጋቢውን ህግ በተመለከተ ያለፈው ፍርድ ቤት የጉዞ እገዳው በከፊል እንዲነሳ በሚል ያሳለፈውን ዉሳኔ ተቀብለዋል፡፡

የኋይት ሀውስ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት አዋጁ ሃገራችንን ለመጠበቅ እና የሃገራችንን ብሔራዊ ደህንነት ሙሉ በሙሉ ለማስከበር የሚያስችለው ነው። ሕጋዊው አዋጅ ለሽብርተኝነት ስጋት ከሆኑ ሀገራት የሚመጡትን ለመገደብ የተወሰነ መሆኑን ገልጸዋል።

Share this post

Post Comment