የአርበኞች ግንቦት 7 የነፃነት የትጥቅ ትግል እርምጃወችና የህወሓት ጉጀሌ ቡድን አሻጥሮች

Source: http://amharic.abbaymedia.com/archives/27396

የአርበኞች ግንቦት 7 የነፃነት የትጥቅ ትግል እርምጃወችና የህወሓት ጉጀሌ ቡድን አሻጥሮች

በናትናኤል መኮንን

በሰሜን ጎንደርና ደቡብ ጎንደር አድማሱን ያሰፋው የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የነፃነት የትጥቅ ትግል ከቀን ወደ ቀን ድልን እየተቀዳጀ መሰረቱን በህዝብ ልብ ላይ እየተከለ ይገኛል። አርፎ የማይቀመጠው ጠላት የወያኔ/ ህወሓት ጉጀሌ ቡድን በዚህ ሰዓት የታጋይ አርበኞችን እርምጃ ከህዝብ ድጋፍ ለማራቅ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም።

ከጅምሩ ጀምሮ ወታደሮችን በት/ቤቶች ፣በጤና ጣቢያወች ፣በቀበሌ አስተዳደር ቢሮወች፣በግብርና ፅ/ቤቶች፣ በዘር አቅርቦት አዳራሾች ፣በከተማ አዳራሾች ..ወዘተ መሰል የህዝብ ንብረቶች ላይ ህዝባዊ አገልግሎቶቹን እያስተጓጎለ ያሰፈረው ወያኔ ታጋይ አርበኞች የወያኔን ስርዓት ለመደምሰስ በተነሱ በደፈጣ ወጊያ ደናውን እያሸተቱ ሙትና ቁስለኛ ሲያደርጉት አስከሬናቸውን መልቀም ሲያቅተው ታጋይ ታጣቂወቹ በሚሰነዝሩት ወታደራዊ ጥቃት የህዝብን ንብረት አወደሙ በማለት ህዝባዊ አሳቢ ለመምሰልና ህዝባዊ ድጋፍ ለማግኘት እንዲሁም የነፃነት ታጋይ አርበኞችን ከህዝብ ለመለየት እየኳተነ ይገኛል።

ገና ከምስረታው በመቀሌና በወሎ ባንኮችን ሲዘርፍ የነበረው ወያኔ ዛሬም እንደለመደው የፈጠራ ድራማውን በመስራት ታጋይ አርበኞች ባንክ ሊዘርፋ እያለ በራሱ ሰወች እራሱን እየዘረፈ ህዝባዊ ድጋፍ ለማግኘት የማይሞክረው ማስመሰል የለም። ሌላው ወያኔ የህዝብ ተሽከርካሪወችን ፣የበሽተኛ መርጃ አምቡላንሶችን፣የኤንጂኦ መኪኖችን፣የቤት መኪናወችን የተለያየ የሰሌዳ ቁጥር እየቀያየሩ በመጠቀም ወታደሮችን እያንቀሳቀሰ መሆኑ ታውቋል። ህዝብን በግፍ ሲበድሉ በነበሩ ባንዳወች ላይ ተደጋጋሚ እርምጃ እየተወሰደባቸው ባለበት ሁኔታ ባለሀብቶች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እያለ ለመንዛት ይዳዳዋል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት የነፃነት ታጋይ አርበኛ ፋኖ ነበልባሎች የወያኔ ሰራዊት ባለበት ሁሉ ጥቃት እየሰነዘረ ይገኛል።
በመጋቢት 11 /2009 ዓ.ም በደቡብ ጎንደር ሊቦ ከምከም ወረዳ ሊቦ ቀበሌ ፈንድቃ በተባለው ቦታ ላይ በጤና ጣቢያ እና ት/ቤት ውስጥ ሰፍሮ የአከባቢውን ነዋሪ የቤት እንስሳት እያረደ እየበላ ና ሴት እህቶቻችን እየደፈረ በነበረው የወያኔ ሰራዊት ላይ እርምጃ ወስዷል።

ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ምግብ ታበላላችሁ በሚል የፈጠራ ምክንያት እያሰረና ንብረት እየዘረፈ በነበረው የወያኔ ወታደር ላይ የህዝብ አጋር የሆነው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋይ አርበኞች ምሽት 6፤00 ሰዓት ሲሆን በወሰደው የማጥቃት እርምጃ በስፍራው ከነበረው የወያኔ ወታደር ላይ የግድያ እርምጃ ወስዷል። በዚህ ዘመቻ በት/ቤቱና በጤና ጣቢያው ላይ ለደረሰው ጉዳት ተጠያቂው የወያኔ ስርዓት ለመሆኑ የሚካድ ሃቅ አይደለም።

የግል ተሽከርካሪ ባለንብረቶች በተለይ
-ከጎንደር፣ አምባጊዮርጊስ ፣ ገደብየ ፣ ዳባት ፣ ደባርቅ ፣ አድርቃ ባሉ መስመሮች
– ከጎንደር ጭልጋ ፣ነጋዴ ባህር ፣መተማ።
-ከጎንደር – ቆላድባ ፣ጯሂት ፣ አለፋ ፣ደልጊ ፣ ቋራ ከጎንደር ማክሰኝት ፣ እፍራንዝ ፣ አዲስ ዘመን ፣ ወረታ ፣ባህር ዳር
-ከጎንደር ማክሰኝት ፣ ደጎማ ፣ በለሳ ፣አርባያ
-ከጎንደር አዲስ ዘመን፣እብናት፣ጉሀላ
-ከጎንደር ወረታ፣ደብረታቦር፣ክምር ድንጋይ፣ ጋሳይ፣ ጋይንት፣ጨጨሆ
-ከጎንደር ትክል ድንጋይ፣ሳንጃ፣ሰሮቃ ዳንሻ፣ሁመራ ከጎንደር ሳንጃ፣አብርሀጅራ፣ኮርኡመር
ባሉ መስመሮች የሚሰሩ አሸከርካሪዎች የወያኔ ወታደሮችን እንዳይጭኑ እናሳስባለን።
ድል ለአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል!!
ሞትና ውድቀት ለወያኔ ጎጀሌ!! —

Share this post

One thought on “የአርበኞች ግንቦት 7 የነፃነት የትጥቅ ትግል እርምጃወችና የህወሓት ጉጀሌ ቡድን አሻጥሮች

Post Comment