የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች የህወሃት አገዛዝ ላይ የከፈቱትን ጥቃት መቀጠላቸውን ገለጹ

Source: http://amharic.abbaymedia.com/archives/27444

ትናንት መጋቢት 15 ቀን የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች  በሰሜን ጎንደር ደንቢያ ወረዳ  ቆላድባ ከተማ  በሚገኘው አማራ ብድር እና ቁጠባ / ተቋም ላይ ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች እርምጃውን ከወሰዱ ቦኋላ ለጸጥታ ሥራ በስፍራው ተሰማርቶ ከነበረው የወያኔ ሠራዊት ጋር እስከ ንጋት ድረስ የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ እንዳደረጉ የገለፁ ሲሆን በጥቃቱ 2 የህወሀት ወታደሮች ተገድለው  በረካቶች  ቆስለዋል ብለዋል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ዒላማ የሆነው የአማራ ብድር እና ቁጠባ በመባል የሚታወቀው ድርጅት ወያኔ ኢህአዴግ ህብረትሰቡን ከሚያሰቃይበት አንዱ እንደሆነና በእርሻ ሥራ የሚተዳደር ገበሬ ያለውዴታው ማዳበሪያ በብድር እንዲወስድ በማስገደድ እስከነወለዱ የሚያስከፍልና በዚህም ከፍተኛ ትርፍ የሚያግበሰብስ እንደሆነ ይታወቃል። በአማራ ብድርና ቁጠባ ስም ህወሃት ከፍተኛ ትርፍ የሚያግበሰብስበት ይሄው ድርጅት ከአርሶ አደሮች በተጨማሪ ሥራ ዕድል ለመፍጠር ለሚፈልግ ሰው ገንዘብ በማበደር 12 በመቶ ወለድ የሚቀበል እና በሰበብ አስባቡ የተበደራችሁትን በጊዜ አልከፈላችሁም በሚል ሰበብ ሀብትና ንብረታቸውን በመውረስ የሚታወቅ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ውስብስብና አስቸጋሪ በሆነ የብድር አሰጣጥ ለአርሶ አደሮች በግዴታ በሚሰጥ የማዳበሪያ ዕዳ የበርካታ ገበሬዎችን የእርሻ በሬ እና የቤት እንስሳቶችን ሳይቀር  እነዲሸጥና እዳውን እንዲከፍል እያደረገ ህዝቡን ባዶ እጁን እያስቀረ ያለ ድርጅት መሆኑን የአካባቢው ህዝብ ይናገራል። ለአማራ ህዝብ ከፍተኛ ጥላቻ ያለው የህውሀት አገዛዝ  የአማራውን ህዝብ በድህነት እያማቀቀ ለመግዛት በብድርና ቁጠባ ሥም የተቋቋመው  ይህ ድርጅት ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳለው ይታወቃል።

በአማራ ክልል ተቋቁሞ ለህወሃት ተመሳሳይ አገልግሎት እያበረከተ ያለው ሌላው ድርጅት የደደቢት ብድርና ቁጠባ የሚባል ተቋም ነው።  የደደቢት ብድርና ቁጠባ ጽ/ቤት በክልሉ ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች እና ለስርአቱ አጋዥ ለሆኑት ግለሰቦች ያለምንም ቅድሜ ሁኔታና የዋስትና መያዣ የሚፈልጉትን ያህል መጠን ገንዘብ የሚያበድር ብቻ ሳይሆን ተበዳሪዎች የተበደሩትን ዕዳ በኪሳራ ምክንያት መክፈል ባይችሉ እንኳ ሌላ ተጨማሪ ብድር በመስጠት እንዲያገመግሙ የሚያደርግ እንደሆነ ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች ይናገራሉ።

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የአማራ ብድርና ቁጠባ  ተቋም ግን ገንዘብ ለማበደር የሚጠይቀው የዋስትና መጠን ከሚሰጠው ገንዘብ ጋር ፍጹም የማይቀራረብ  እንደሆነ እና አላማውም በብድር ሥም ተበዳሪዎችን ለመበዝበዝና ለማደህየት መሆኑን ህብረተሰቡ በምሬት  ይገልጻል።የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በህብረተሰቡ ዘንድ እጅግ ከሚጠሉ የኢፈርት ድርጅቶች አንዱ ነው። የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች እርምጃ የወሰዱበትም በዚህ ምክንያት ነው።

 

Share this post

One thought on “የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች የህወሃት አገዛዝ ላይ የከፈቱትን ጥቃት መቀጠላቸውን ገለጹ

  1. Ye amaharan geberie ke derito ena kemal yalakekew be tplf tigel aydelem woy? Yehe yetemeketegna zebatelo worie new. Yehen yebualt demamit mafenedat tetachehu merit lay teb yemil andet neger biteseru yeteshale new. Bualetegoch !!!

    Reply

Post Comment