የአርባ ቀን መታሰቢያ ለአርሲና ባሌ ሰማእታት

ሁለት ቦታ ቀብርህ ቀብርህ ሁለት ቦታ የት ይቁም ሐውልትህ ተዝካርህ የት ይሁን አመድ ሆኗል ቤትህ ዝክሩን ማን ይደግስ ታርደው ልጅ እናትህ ቀብርህ ሁለት ቦታ ደም ሥጋ አጥንትህ ከፊሉ ጅብ ሆድ ውስጥ ከፊሉ ጉድጓድ ውስጥ የት ይቁም ሃውልትህ? በምድር አልተመቸም በኢዮር ይደረግ አርባና ፍታትህ። አርባህን ማን ያውጣ? ሞትህ በገጀራ ፍታትሕ ባሞራ ቀብርህ በጅብ ጎሬ ርስትህን ሊቀሙ ማተብክን እያዩ ያረዱህ ገበሬ። አርባህ ነገ ማልዳ ማን ያወጣልሃል ሚስትህ ልጅህ ታርዳ? ወገን ያልከው ነስቶህ በገዛ ሃገርህ መቀበሪያ ጉድጓድ ከውቅያኖስ ማዶ ሐዘን እንድረስህ እንባችን ውቅያኖስ ለቅሷችን ነጎድጓድ አንተም ቋሚው ምዉት ተንቀሳቃሽ በድን እኩልህ ተገድሏል እኩልህም ቢድን ሰማንያህ ተቀዳ ቆንጨራው ሲቃጣ አርባዋን አወጣህ አርባህን ማን ያውጣ

Source: Link to the Post

Leave a Reply