የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል የተባሉት እነግርማ ካሳን ጨምሮ ለ11 የፖሊስ አመራሮች ዋስትና ተፈቀደ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/43633


ፍርድ ቤቱ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳን ጨምሮ ለ11 የፖሊስ አመራሮች ዋስትና ፈቀደ
በአዲስ አበባ ሰኔ 16 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ላስመዘገቧቸው ለውጦች በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በመስቀል አደባባይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው በሚል ምርምራ እየተካሄደባቸው የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ ዋስትና ተፈቀደላቸው።
አቃቤ ህግ ምክትል ኮሚሽነሩን ጨምሮ ሌሎች 11 የፖሊስ አመራሮችም በዋስ ቢለቀቁ እንደማይቃወም ትናንት ማስታወቁ ይታወሳል።
የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎትም ዛሬ ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ፈቅዷል።
ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም፣ ኮማንደር ገብረስላሴ ታፈረ፣ ኮማንደር ግርማይ በርሄና ኮማንደር አንተነህ ዘላለምን ጨምሮ ሌሎች የአሰራር ክፍተት አሳይተዋል ተብለው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.